የእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ፣ የእነ ፕሮፌሰር ዝናቡ ዋስትና አልተከበረም
ረቡዕ፣ ሰኔ 12 2016የእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደረገ
የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ዮሃንስ ቧያሌው 1ኛ ተከሳሽ በሆኑበት የክስ መዝገብ ሥር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስትያን ታደለ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ዶክተር ካሳ ተሻገርን ጨምሮ የጋዜጠኞችና የሌሎችንም የክስ መዝገብ የሚመራው የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፤ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄው ውድቅ አድርጓል፣ የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ ለማድመጥ ደግሞ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን ከጠበቆቻቸው አንደኛው ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።እሥር ፣ የሽብር ክስ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማብቃት
ባለፈው ሳምንቱ ችሎት ከተከሳሾች መካክል አቶ ዮሃንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስትያን ታደለ ማንነትን መሰረት ያደረገ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸው መሆኑን፣ በዚህም የሕሊና ጉዳት እንደሚደርስባቸው እና በአማራነታቸው ምክንያት ከሌሎች ታራሚዎች በተለየ መብታቸው እየተጣሰ መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ በማረሚያ ቤቶቹ አስተዳደሮች ላይ ተገቢ ቅጣት እንዲጥል ጠይቀው ነበር።
የእነ ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ የተፈቀደ ዋስትና ይግባኝ ተጠይቆበታል
የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ በአዋሽ አርባ ታሥረው ቆይተው ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩ ዘጠኝ ሰዎች በገንዘብ ዋስትና ከእሥር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ሰኞ እለት የወሰነ ቢሆንም ፌዴራል ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ለአርብ ቀጠሮ ሰጥቷል። የአቶ ታዬ ደንደዓ እና የእነ ቀሲስ በላይ የችሎት ውሎ
የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ዛሬ ለዶቼ ቬለ እንዳሉት፤ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የወሰነላቸው ዘጠኙ ሰዎችን ከእሥር እንዲወጡ ለዋስትናው የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍለው ነበር።
በሌላ በኩል በእነ ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ ሰዎች ትናንት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ሲሆን፣ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ አሻሽሎ እንዲቀርብ በሚል ለሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል።በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 51 ተከሳሾች ችሎት
ለበርካታ ወራት በእሥር ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችን ጨምሮ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች መካከል የተወሰኑት መፈታታቸውን በበጎ እንደሚመለከተው የገለፀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተማጋቾች ማዕከል፤ መንግሥት የተፈፃሚነት ጊዜው ባበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት "አለአግባብ በሰብዓዊ መብት ሥራቸው ምክንያት በእሥር የሚገኙትን ጋዜጠኞች ጨምሮ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን በሙሉ እንዲፈታ" እና ሀሳብን በነፃነት የመግለጽ እና ሌሎች መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚያስችል የፖለቲካ እና የሲቪክ ምህዳር እንዲፈጠር የድርሻውን እንዲወጣ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ