1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የሰላም ጥሪ

ረቡዕ፣ መስከረም 2 2016

የኦሮሚያ ክልልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአዲሱ 2016 ዓ.ም ከሰላም አማራጭ ውጪ የሚደረግ ትግል “ለህዝባችንም ሆነ ለማንም አይፈይድም” ብለዋል፡፡ የመንግስታቸውም መንገድ ሰላማዊ መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ በክልሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚንቀሳቀሱ ያሏቸው ልዩነቶችን በውይይት እንዲፈቱም ጠይቀዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4WITr
አቶ ሽመልስ በዚሁ መልእክታቸው በማህበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች መኖሩ የሚያስገርም አለመሆኑንም አስረድተዋል። ልዩነቶችንም
ፖለቲከኞቹ እደሚሉት ግን የጥሪው ገቢራዊነት ላይ ጥርጣሬ አላቸው፡፡ አቶ ደስታ የቀረበው ጥሪ ከቃላት የዘለለ ስራ የሚያስፈልገው እንደመሆኑ በተግባር ሊታገዝ ይገባል ሲሉ፤ አቶ ጥሩነህ በዋናነት ልነቶቻቸውን ለማጥበብ የሚፈልጉ አካላት ድጋፍ እንኳ የሚጠይቁ ከሆነ መልካም አበርክቶ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የሰላም ጥሪ

ትናንት በባተው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የኦሮሚያው ግጭት በሰላም እንዲደመደም  ሁሉም አካላት እንዲዘጋጁ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ፡፡ አቶ ሽመልስ የአዲሱን ዓመት አቀባበል በማስመልከት በክልሉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ(OBN) ባደረጉት የቀጥታ ስርጭት ንግግር መገዳደሉ ይብቃ ብለዋል፡፡ በዚህ ላይ ለዶቼቬለ  አስተያየት የሰጡ ፖለቲከኞችም ጥሪውን ደግፈው፤ ለገቢራዊነቱም የተሻለ ስራ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡
“2016 ዓ.ም. የእርቅ ዘመን ነው፡፡ የክልላችን መንግስት ሁሉም የህዝባችን ጥያቄ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ይስተናገዳል የሚል ጠንካራ እምነት አለው፡፡ በግጭት ለሚባክን ጊዜና ሃብት ቦታ የለንም፡፡ ለሰከንድም ቢሆን ከሰላማዊ መንገድ ውጪ ህዝባችንን አሸናፊ ያደርጋል ብዬ የማስበው መንገድ የለም፡፡ እንደከዚህ ቀደሙ አሁንም በምናደርገው ጥሪ 2016 በኦሮሚያ የመሳሪያ ድምጽ የሚዘጋበት፣ ወንድም ወንድሙን የሚገድልበት ሳይሆን ሰላም ሰፍኖ የህዝባችን አንድነት በእርቅ ከፍ ወዳለ ደረጃ የሚሻገርበት፤ ያለውን ልዩነት በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ የምንፈታበት እንዲሆን በድጋሚ ጥሪዬን ለማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡”ለኦሮሚያ ግጭት የሰላም አማራጭ ጥሪ
የኦሮሚያ ክልልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለአዲሱ 2016 ዓ.ም. አቀባበል በቢሾፍቱ በተሰናዳው የዋዜማ ፕሮግራም የተናገሩት ነው፡፡ አቶ ሽመልስ በዚሁ መልእክታቸው ከሰላም አማራጭ ውጪ የሚደረግ ትግል “ለህዝባችንም ሆነ ለማንም አይፈይድም” ብለዋል፡፡ የመንግስታቸውም መንገድ ሰላማዊ መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ በክልሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚንቀሳቀሱ ያሏቸው ልዩነቶችን በውይይት እንዲፈቱም ጠይቀዋል፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች መኖሩ የሚያስገርም አለመሆኑንም በማስረዳት ልዩነቶችን በማጥበብ ሰላምን በማስፈን ረገድ ለባህላዊ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶችም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ከዚሁ ሃሳብ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደስታ ድንቃ ለዶይቼ ቬለ እንደነገሩት፤ የሰላም ጥሪው ተቀባይነት ያለው የዓመት በዓሉ ጥሪ እንደመሆኑ እሳቸው የሚመሩት ምክር ቤት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡ “ጥሪው በጣም ተቀባይነት ያለው ጥሪ ነው፡፡ ምክር ቤታችንም ጥሪውን በአዎንታዊነት የሚመለከተው ነው” ብለዋል፡፡
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሃፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ በፊናቸው በዚሁ ላይ በሰጡን አስተያየታቸው ጥሪውን እንከን የለሽ ብለውታል፡፡ “እንደዚህ አይነት የእርቅ ጥሪ እንኳን ከሰው ሴይጣንም እርቅ አወርዳለሁ ብሎ ብነሳ ድጋፍ ነው የምንሰጠው፡፡”አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጡ 
ፖለቲከኞቹ እደሚሉት ግን የጥሪው ገቢራዊነት ላይ ጥርጣሬ አላቸው፡፡ አቶ ደስታ የቀረበው ጥሪ ከቃላት የዘለለ ስራ የሚያስፈልገው እንደመሆኑ በተግባር ሊታገዝ ይገባል ሲሉ፤ አቶ ጥሩነህ በዋናነት ልነቶቻቸውን ለማጥበብ የሚፈልጉ አካላት ድጋፍ እንኳ የሚጠይቁ ከሆነ መልካም አበርክቶ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡
ለኦሮሚያው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት የኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሚያ በስፋት በትጥቅ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር የጀመሩት ድርድር ተቋርጦ ግጭቱ ዳግም በስፋት ማገርሸቱ አይዘነጋም፡፡ 

አቶ ሽመልስ የአዲሱን ዓመት አቀባበል በማስመልከት በክልሉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ(OBN) ባደረጉት የቀጥታ ስርጭት ንግግር መገዳደሉ ይብቃ ብለዋል፡፡ በዚህ ላይ ለዶቼቬለ  አስተያየት የሰጡ ፖለቲከኞችም ጥሪውን ደግፈው፤ ለገቢራዊነቱም የተሻለ ስራ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡
ትናንት በባተው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት የኦሮሚያው ግጭት በሰላም እንዲደመደም  ሁሉም አካላት እንዲዘጋጁ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ምስል Seyoum Getu/DW

ሥዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ