1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩስያ ገብቷል ስለመባሉ

ገበያው ንጉሴ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 19 2017

የስሜን ኮሪያና ሩሲያ ወታደራዊ ስምምነት እንዳላቸውና ስሜን ኮሪያም ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እርዳታ እንደምታደርግ ሲነገር የቆየ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት ተዋጊ ወታደሮች ወደ ሩሲያ ምምጣታቸው ግን ጦርነቱን ይልቁንም ካውሮፓ ውጭ ጭምር እንዳያሰፋው አስግቷል ።

https://p.dw.com/p/4mN7N
Nordkorea Besuch von Russlands Präsident Putin
ምስል Vladimir Smirnov/POOL/TASS/dpa/picture alliance

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩስያ ገብቷል ስለመባሉ

የሰሜን ኮሪያ ወታደደራዊ እርዳታ  ለሩሲያ

ሰሜን ኮሪያ ከሁለት አመት በፊት በዩክሬይን ላይ ጦርነት የከፍተችውን ሩሲያን ለመርዳት ተዋጊ ወታደሮችን የላከች ስለመሆኑ በሰፊው እየትነገረ ነው።  የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ናቶ ዋና ጸሀፊ ማርክ ሩተ  ትናንት እዚህ ብራስልስ በሰጡት መግለጫም ይህንኑ ቀደም ብሎ በዩክሬንና  አሜርካ ወታደራዊ ምንጮች ሲነገር የቆየውን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ መገኘት አረጋጠዋል “ዛሬ የስሜን ኮሪያ ወታደሮች ወደ ሩሲያ የተለኩ መሆኑን አረጋግጣለሁ በማለት ወታደሮቹም በሩሲያ የኩርስክ ክልል የሰፈሩ መሆኑን ገልጸዋል ።

ወታደራዊ እርዳታው የፈጠረው   

የስሜን ኮሪያና ሩሲያ ወታደራዊ ስምምነት እንዳላቸውና ስሜን ኮሪያም ለሩሲያ የጦር መሳሪያ እርዳታ እንደምታደርግ ሲነገር የቆየ ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት ተዋጊ ወታደሮች ወደ ሩሲያ ምምጣታቸው ግን ጦርነቱን ይልቁንም ካውሮፓ ውጭ ጭምር እንዳያሰፋው አስግቷል ። የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ መገኘት ደቡብ ኮሪያንም ከዩክሬን ባላነሰ ሁኔታ ያሳሰባት መሆኑ እየተሰማ ነው። ሰሜን ኮሪያና ደቡብ ኮሪያ በተጻራሪ ቆመውና ተፋጠው የሚገኙ ሀይሎች መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጎን ቆመች እንደሚባለው ሁሉ፤ ደቡብ ኮሪያም ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ በማድረግ  ከዩክሬን ደጋፊ ምራባውያን ሀይሎች ጎን ተሰላፊ ነች ነው የሚባለው።  ሰሜን ኮሪያ ወታደሮቿን ከሩሲያ ጎን ስታሰልፍ፤ ሩሲያ በበኩሏ የሰሜን ኮሪያን ወታደራዊ ሀይል ለማጠናከርና  የኒውክለር ፕሮግራሟን እንድታሳድግ ልታገዝ ስለምትችል ነው፤ የደቡብ ኮርያና የአካባቢው የኢንዶ ቻይና አገሮች የስጋት ምንጭ።የኔቶው ዋና ጸሀፊ  ማርክ ሩተ መግለጫም ይህንኑ ስጋት የሚያጠናክርና የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩስያ ጎን መቆም የጦርነቱን ደረጃ ከፍ የሚያደርገውና የሚያሰፋው መሆኑን የሚገልጽ ነው። የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ መገኘትና በጦርነቱ መሳተፍ ምን ማለት እንደሆነ ሲያብራሩም፤   “ አንደኛ  ህገወጡን የሩሲያ ጦርነት ማጠናከር ነው፤ ሁለተኛ የመንግስታቱ ድርጅትን የጸጥታ ምክርቤትን ውሳኔ መጻረር ነው፤  ሶስተኛ ሩሲያ የከፈተችውን ጦርነት እንዲሰፋ የሚያይደርግ ነው” በማለት ኔቶ ሩሲያና ሰሜን ኮሪያ ከእንደዚህ አይነት እሳቸው ህገወጥ ካሉት እርምጃ ይቆጠቡ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።  

የምራብውያን አገሮች የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ መገኘት ላይ   

የውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኑነ ሀላፊ ሚስተር ቦርየል  ቀደም ሲል በሀያ ሰባቱ አባል አገሮች ስም ባወጡት መግለጫ  ስሜን ኮሪያ  የሩሲያን ህገወጥ ጦርነት ለማገዝ ወታደሮችን መላኳን  አውግዘዋል፤ ድርጊቱን አለማቀፍ ህግን የሚጥስና የአውሮፓና የአለምን  ሰላም የሚያናጋ ነው  በማለትም አባል አገሮች  ለዩክሬይን የሚስጡትን እርዳታ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል ።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንም ይህንን የስሜን ኮርያን እርምጃአደገኛ በማለት ስጋታቸውን መግለጻቸው ታውቋል፡፤።የአሜርካ መከላከያ ዲፓርሜንት ‘ፔንታጎን” ቃል አቀባይ ሳብሪና ሲንግ  “ከእንግዲህ ዩክሬን የአሜሪካንን  መሳሪያ በሩሲያ መሬት ላይ እንዳትጠቀም የተጣለው ገደብ  ላይኖር ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።  ቃል አቀባዩዋ  ይህን የፕሬዝዳንት ፑቲንን ስሜን ኮሪያን  ወታደሮችን የማሰለፍን  እርምጃ የተስፋ መቁረጥ እርምጃ ብለውታል። “ ይህ እርምጃ የሚያሳየው የፕሬዝዳንት ፑቲንን ተስፋ መቁርጥና በጦርነት አሳካዋላሁ ያሉት ዕቅድ ሊሳካ ያለመቻሉን ነው” በማለት እሳካሁን በጦርነቱ ያለቁባቸውን  ከአምስት መቶ ሺ በላይ ወታደሮች ለመተካት ያለባቸውን ችግር የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል።

የስሜን ኮሪያ ወታደሮች በጦርነቱ መሳተፍ ጦርነቱን  መቀየር መቻል አለመቻሉን ግን ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኖ መናገር እንደማይቻል ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።
የስሜን ኮሪያ ወታደሮች በጦርነቱ መሳተፍ ጦርነቱን  መቀየር መቻል አለመቻሉን ግን ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኖ መናገር እንደማይቻል ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።ምስል Russian President Press Office/dpa/picture alliance

የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በጦርነቱ ለውጥ ያመጡ ይሆን?

የስሜን ኮሪያ ወታደሮች በጦርነቱ መሳተፍ ጦርነቱን  መቀየር መቻል አለመቻሉን ግን ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኖ መናገር እንደማይቻል ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት። የሴሜን ኮሪያ ወታደሮችን ልምድ ማነስና የቁንቋ ችግር በመጥቀስ ውጤማነታቸውን  የሚጠራጠሩ ያሉትን ያህል፤ ወታደሮቹ ልዩ ስልጠና ያላቸውና ተጨማሪ ስልጠና የሚሰጣቸው በመሆኑ አስተዋጿቸው ቀላል እንደማይሆን የሚናገሩም አሉ።፡ በለንደን ኪንግ  ኮሌጅ ወታደራዊ ተንታኝ የሆኑት ማሪና ሚሮን፤ እነዚህ ወታደሮች በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑና ለልዩ ተልኮ የተዘጋጁ መሆኑን ይገልጻሉ፤ “ የምንነጋገረው  ልዩና በክፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ወታደሮች ጉዳይ ነው። ስሜን ኮሪያ እነዚህን የመሰሉ ልዩ ስልጠና የወሰዱ  ሁለት መቶ ሺ ወታደሮች ያሏት ሲሆን አሁን የመጡት ጥቂቶቹ ናቸው” በማለት በአሁኑ ወቅት ወደ ሩሲያ የተላኩት አስር ሺ ያህል እንደሆኑንና በቀጣይም ሌሎች ሊላኩ እንደሚችሉ አመላክተዋል

 ሩሲያ ሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን በማስለፏ እየተነሳባት ባለው ክስ

ሩሲያ የስሜን ኮሪያ  ወታደሮች በአገሯ መገኘታቸውን ባታምንም አላስተባበለችም። ይልቁንም የስሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን አገሮች ድርጅት “ኔቶ”ና ያውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የሚሰጡት ድጋፍ በጦርነቱ በቀጥታ የመሳተፍ ያህል ነው በማለት ከስሜን ኮሪያ ጋር ያለው ወታደራዊ ዊ ግንኙነትም በዚህ አግባብ መታየት እንዳለበት እያሳሰብች ነው።

ከዩክሬን ጎን የቆሙት የስሜን አትላንቲክ ድርጅት ኔቶና ያውሮፓ ህብረት ለዚህ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ተሳትፎ የሚስጡት ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይደለም።
ከዩክሬን ጎን የቆሙት የስሜን አትላንቲክ ድርጅት ኔቶና ያውሮፓ ህብረት ለዚህ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ተሳትፎ የሚስጡት ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይደለም። ምስል Korean Central News Agency/Korea News Service/AP/picture alliance

የዩክሬን ደጋፊ አገሮች አሁናዊ አጸፋ ምን ሊሆን ይችላል?

ከዩክሬን ጎን የቆሙት የስሜን አትላንቲክ ድርጅት ኔቶና ያውሮፓ ህብረት ለዚህ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ተሳትፎ የሚስጡት ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አይደለም። የዩክሬን  ፕሬዝድንት ሚስተር ዘለንስኪ ግን የሰሜን ኮሪያና ሩሲያ ወታደራዊ ጥምረት የአለም ጠርነት መጀመር የመጀመሪይ እርምጃ ነው በማለት በቀጥታ ከዩክሬይን ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ ሲያደርጉ ነው የሚሰሙት። የኔቶና የህብረቱ አገሮች ግን በቀጣይ ቢያንስ ዩክሬይን ያገ|ኘችውን የጦር መሳሪያ በሩሲያ ላይ እንዳትጠቀም የጣሉትን ገደብ ሊያነሱ ይችላሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ሩሲያ በዩክሬይን ላይ የከፍተችው ጦርነትና ይህን በመቃወም ከሩሲያ አንጻር የተሰለፉት የምራብ ሀይሎች ያሉበት ሁኔታና የሚታየው የሀይል አሰላልፍ የአውሮፓን  ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ የአለምን ሰላም ከስጋት ላይ የጣለ ስለመሆኑ በሰፊው ነው የሚነገረው።  ቀድሞ የብርታኒያ የጦር ሀይሎች ዋና አዛዥ የነበሩት ጀነራል ሰር ፓትሪክ ሳንደርስ ለቢቢስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ አለም ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ ያገቸውን ስላም እንዳታጣ ያሰጋ ሲሉ እው ለቢቢሲ በሰጡት ቃለመጠይቅ ሲናገሩ የተሰሙት፤

“አሁን የሚታየው የሩሲያ ቻይና  ኢራንና ስሜን ኮሪያ  ጥምረት በድንገት ወደ ከፍኛ  ጦርነት ለመግባት የሚያስችል አደገኛ ሁኔታ ነው። ምክንያቱም እስከአሁን የአለምን ሰላም አስጠብቆ ያቆየው አለምአቀፋዊ ሥርአት በማብቃቱ ነው” በማለት ወቅቱ ልዩ ታሪካዊ ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።

እናም አውሮፓ ከመቼውም ግዜ ይበልጥ  አሁን  ከደቡብ በመካከልኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት ሊያጥለቀልቃት በሚችል ስደተኛ፤ ከሰሜን ደግሞ በሩሲያ ዩክሬይን በኩል ሊመጣ በሚችል  ሁሉ አቀፍ ጦርነት ተወጥራ ተይዛለች ነው የሚባለው። በዚህ መሀል ከቀናት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ በተለይ ፕሬዝዳንት ትሩምፕ ካሸነፉ ቢያንስ የሩስያ ዩክሬይን ጦርነት ሊበርድ ይችላል በማለት በተስፋ የሚጠብቁም አሉ።

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር