1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ፍተሻ የአለም ሐያላን ትኩረትና የአለም ሰላም

ሰኞ፣ ግንቦት 24 2001

ዴን ረስክና ቻርልስ ቦኔስትል ካርታቸዉን ዘረጉ።እሁለት አሰመሩበት።ነሐሴ 10 1945 ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።ትዕዛዝ ተፈፀመ።ፀደቀም።

https://p.dw.com/p/I1ZY
ኪም ጆንግ ኢል-የሰሜን ኮሪያ መሪምስል AP

ሁለቱ የአሜሪካ ወጣት መኮንኖች የታዘዙትን ከማስፈፀም ባለፍ የኮሪያ ልሳነ ምድር ሕዝብ ፍላጎትን ለመጠበቅ፤ ታሪኩን ለማወቅ፣ የእርምጃቸዉን መዘዝ ለማጤን ብስለት-ብልሐቱ፣ሥልጣን-ሐላፊነቱም አልነበራቸዉም።የጃፓን ጠላቶቹን እየወቀጠ ወደ ደቡብ የሚተመዉ የሶቬት ሕብረት ጦር ኮሪያ-ወገብ ላይ ሲደርስ ግስጋሴዉን የገታበት ምክንያት ደግሞ ለመኮንኖቹ አይደለም ለአለቆቻቸዉም ሚስጥር ነበር።ዴን ረስክና ቻርልስ ቦኔስትል ካርታቸዉን ዘረጉ።እሁለት አሰመሩበት።ነሐሴ 10 1945 ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።ትዕዛዝ ተፈፀመ።ፀደቀም።መዘዙ-በሚሊዮች ሕይወት፣ በአመታት ሂደት ያለመዘዙ ዚቅ፤ ዛሬ ኑክሌር የማማዘዙ ጭንቅ ነዉ-ያፍታ ቅኝታችን ሰበብ።

dw,wikipedia

Negash Mohammed