አማራ ክልል አንፃራዊ ሠላም ሠፍኗል-ርዕሰ መስተዳድር
ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2015ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ታጣቂ ኃይላት ሲዋጉባቸዉ በነበሩት በአብዛኖቹ የአማራ ክልል አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታወቁ።ርዕሠ መስተዳድር አረጋ ከበደ የርዕሠ መስተዳድርነቱን ሥልጣን ከያዙ ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት የመንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች የክልሉን የዞን ከተሞች በሙሉና አብዛኞቹን የወረዳ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል። የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች ግን የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ አገልግሎት መጪያ ተቋማና መንገዶች ተዘግተዉ ሠላም ሠፍኗል ማለት አይቻልም ይላሉ።የአማራ ክልል ውጊያ ወቅታዊ መረጃ
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ