በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የወደብ ሃሳብ ሰዎች ምን አሉ?
ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2016ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቀይ ባሕር እና በአካባቢው ካሉ ወደቦች የባሕር በር የማግኘት መብቷ እንዲረጋገጥ ጉዳዩ የሕዝብ መወያያ እንዲሆን ሰሞኑን ያቀረቡት ሀሳብ ብዙ እያነጋገረ ነው። "የቀይ ባሕር ጉዳይ በደንብ ንግግር ያስፈልገዋል" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ቀይ ባሕር እና ዓባይ ኢትዮጵያን የሚበይኑ፣ ከኢትዮጵያ የተቆራኙ፣ ለኢትዮጵያ እድገትና ጥፋት መሠረት ናቸው" ሲሉ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ተናግረው ነበር።አሰብ ደርሶ መልስ ይህንን ለማሳካት አካሄዱ "በተቻለ መጠን በሰላማዊ መንገድ" መሆን እንዳለበት ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፌደሬሽን፣ ኮንፌደሬሽን ወይም የመሬት ልውውጥ አማራጭ የውኃ በር ማግኛ አማራጮች መሆናቸውን ዘርዝረዋል።
ኢትዮጵያ የምትገለገልበት ወደብ የማግኘት ጉዳይ መሠረታዊ መሆኑን የጠቀሱት አስተያየት ሰጪዎቹ ይሁንና ይህ ጉዳይ በቀላሉ ሊሳካ የሚችል ነው ብለው እንደማያምኑ ገልፀዋል።የኤርትራ አፋሮች ጥሪና የፖለቲካ ጥያቄ
ከ30 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ይህንን ወደብ የማግኘት መብቷን ተገቢ ባልሆነ መንገድ ማጣቷን የገለፁ አንድ አስተያየት ሰጪ ይህ ጉዳይ አሁን መነሳቱ አሁን ወቅቱ ነው ወይ የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ እንዳደረጋቸውም ገልፀዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የተወሰኑ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ሀሳባቸውን ጠይቀናቸዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ