1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካኬንያ

ኬንያ- የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አንደኛ ዓመት የስልጣን ዘመን

ሰኞ፣ መስከረም 7 2016

ስልጣን ከያዙ አንድ ዓመት የደፈኑት የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ የምግብ ዋጋ እና የግብር ክፍያ በማሻቀቡ የሩቶ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ቁጣቸዉን መግለጽ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ፕሬዚዳንት ዊሊያም ወደሥልጣን እንዲመጡ ድምጽ የሰጠላቸዉን ሕዝብ የሚያዳምጥ ጆሮ የላቸዉም ሲሉ ምሁራን ቅሬታቸዉን እየገለጹም ነዉ።

https://p.dw.com/p/4WPNe
William Ruto Kenia  Africa Climate Summit
ምስል Khalil Senosi/AP/picture alliance

"የዊሊያም አስተዳደር የፖለቲካ ቁማሩን ትቶ ትኩረቱን ህዝብ ላይ ያድርግ"

ስልጣን ከያዙ አንድ ዓመት የደፈኑት የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በኬንያ የምግብ ዋጋ እና የግብር ክፍያ በማሻቀቡ የሩቶ መንግሥት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ቁጣቸዉን መግለጽ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ፕሬዚዳንት ዊሊያም ወደሥልጣን እንዲመጡ ድምጽ የሰጠላቸዉን ሕዝብ የሚያዳምጥ ጆሮ የላቸዉም ሲሉ ምሁራን ቅሬታቸዉን እየገለጹም ነዉ።   

በርካታ ኬንያውያን ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በመጽሐፍ ቅዱስ ስሙ እንደተጠቀሰዉ ከዜጎች ኪስ የመጨረሻ ሳንቲም በግብር ስም እንደሚሰበስበዉ ዘኪዮስ ሆነዋል ሲሉ "ዛካዮ" የሚል ስምም አዉጥተዉላቸዋል።  ሩቶ የአስተዳደራቸዉን አንደኛ ዓመት ሲያከብሩ በኬንያ ከሚገኙ አንዳንድ ዜጎች ጠንካራ ነቀፊታ አዘል አስተያየትን እየሰጡ ነዉ።

"ሩቶ በሥልጣን ላይ በቆዩበት በዚህ አንድ ዓመት ለአብዛኞቻችን ልንሸከመው የማንችለው ችግር ነዉ የገጠመን" ሲሉ በናይሮቢ ነዋሪ የሆኑት የኮምፒዉተር ባለሞያ ፍሬድ ኦኮ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ሌላዉ የሞምባሳ ከተማ ነዋሪ ሃሚሲ ሰሊምም አስተያየታችዉ እንዲሁ ነዉ የሰጡት። "የዊሊያም ሩቶ አስተዳደር እስከ አሁን በኬኒያ ታሪክ ያልታየ የከፋ ጊዜ ነው"   

ዊሊያም ሩቶ በምርጫ ዘመቻው ራሳቸዉን ለህዝብ የቆሙ አድርገዉ ነበር የቀረቡት።
ዊሊያም ሩቶ በምርጫ ዘመቻው ራሳቸዉን ለህዝብ የቆሙ አድርገዉ ነበር የቀረቡት።ምስል Mosa'ab Elshamy/AP/picture alliance

ባለፈው ዓመት ራሳቸዉን ለሚቸገሩ ተራ ሰዎች እጩ እንደሆኑ አድርገዉ ወደ ሥልጣን የጨበጡትየኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ይህን ያህል በዜጎች ተወዳጅነትን ያጡት እንዴት ይሆን?የኬንያው ተቃውሞና የፕሬዝዳንቱ ዛቻ፤ የደቡብ ሱዳን ተፈናቃዮች

ሩቶ ሥልጣን ከያጡ በኋላ "መንግሥቴ የኑሮ ውድነት ይቀንሳል" ሲሉ ገልፀዉ ነበር። ይሁን እንጂ ከአንድ ዓመት በኋላ ዛሬ በኬንያ ብዙም ለዉጥ አልታየም። እንደብዙዎች እምነት በፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አመራር ሥር ዜጎች የሚገኙት በከፋ ሁኔታ ዉስጥ ነዉ። የኬንያ የፖለቲካ ተንታኝ ፓትሪክ ጋታራ ለዶቼ ቬለ ሩቶ የገቡት ቃል ብዙ ነበር ብለዋል።

"ኬንያ ለምሁራኖችዋ ብቻ ሳይሆን እታች ላሉት ዜጎችዋ ሁሉ የበለጠ እንድትሠራ ለማድረግ ስርዓቱን እንዴት ሊለዉጡ እንደሚችሉ ብዙ ቃል ገብተዉ ነበር። ብዙ በጎ ፈቃድ እንዳላቸዉም አሳይተዉም ነበር። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ በፍጥነት ቃላቶቹ ባዶ እየሆኑ መጡ። ኬንያ ዉስጥ በጣም አስፈላጊ በሆኑ ሸቀጦች ላይ የቀረጥ ጭማሪ ተደርጓል። በምግብ ሸቀጦች እና ነዳጅ ላይ አይደረገም ሲሉ ሲዝቱበት የነበረዉ ያሉት ድጎማንም አስወግደዋል። ይህም ደግሞ ለዋጋ ንረቱ ዋና ምክንያት ሆንዋል። ይህን ተከትሎ ኬንያውያን የኑሮ ውድነት አሳስቦናል ሲሉ ጥያቄያቸዉን ሲያሰሙ ምንም እንዳልሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ እያሉ ነዉ የሚገኙት።"

በኬንያ ከባለፈዉ ነሐሴ ወር ጀምሮ የዋጋ ግሽበት ወደ 6.7% ቀንሷል። ይሁንና ባለፈው ዓመት  የነዳጅ ዋጋ 22%፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋጋ ደግሞ ወደ 50% ጨምሯል። እንደ ስኳርና ባቄላ ባሉ ሸቀጦች ላይ ደግሞ 60% እና በ31% ጭማሪ አሳይቷል።

የኬንያው ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቻቸዉ መንግሥት የኑሮ ውድነት እንዲቀንስ ሀገር አቀፍ ተቃውሞ እንዲያካሂዱ ከጠየቁ በኋላ፤ በአንድ ቦታዎች ሰላማዊ ተቃዉሞዎቹ ወደ ነዉጥ ተለዉጠዉ ነበር። 
የኬንያው ተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቻቸዉ መንግሥት የኑሮ ውድነት እንዲቀንስ ሀገር አቀፍ ተቃውሞ እንዲያካሂዱ ከጠየቁ በኋላ፤ በአንድ ቦታዎች ሰላማዊ ተቃዉሞዎቹ ወደ ነዉጥ ተለዉጠዉ ነበር። ምስል Luis Tato/AFP

ፕሬዚዳንት ሩቶ ባለፈዉ ሐምሌ ወር ባዶ ለሆነዉ የመንግሥት ካዝና ከ2.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚያመጣ የሚጠበቀውን የገንዘብ አዋጅ ፈረመዋል። ይህ አዋጅ እንደ ነዳጅና ምግብ ባሉ መሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ላይ፤ አዳዲስ ግብር መጨመር እና በተንቀሳቃሽ የገንዘብ ዝውውር ላይ እንዲሁም የመኖሪያ ቤት ንድፍ በማውጣት ሥራ ላይ አወዛጋቢ የግብር ክፍያ ማውጣትንም ይጨምራል።

የኬንያ መንግሥት እንደሚለዉ የሚሰበሰበዉ ግብር ለሥራ ፈጠራ እና የሕዝብ ተበዳሪነት ለመቀነስ ይረዳል። ይሁንና አወዛጋቢዉ፤ አብዛኛዉ ዜጋ ኑሮን ለማሸነፍ የእለት ጉርሱን ለማግኘት የሚታገል መሆኑ ነዉ። ወደ 50 ሚሊዮ ህዝብ በሚገኝባት ኬንያ ዜጎችዋ ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ናቸዉ።

«ከ50 ሚሊዮን ሕዝብ ትንሽ በለጥ ብሎ በሚገኝባት ኬንያን ብትመለከቱ፤ አብዛኞቹ ዜጎች የሚኖሩት ከድህነት በታች በቀን ከአንድ ዶላር ያነሰ እያገኙ ነዉ። እንደ ጤና፣ መኖርያ ቤት፣ የመጠጥ ውኃ፣ የኑሮ መሰረታዊ የሚባሉ ነገሮችን ሁሉ ማግኘት አይችሉም።» ሲሉ ሲሉ አስተያየታቸዉን የሰጡት በናይሮቢ ወጣቶችን በማስተዳደር ሥራ ላይ የተሰራዉ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ኔሪማ ዋኮ ናቸው።የኬንያው ፕሬዝደንት የጀርመን ጉብኝት እና ማሳሰቢያ

ታዋቂዉ የኬንያ የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ አዲሱህግ፤ ኬንያውያን ሊሸከሙት የማይችሉት ስህተትና ሙከራ ነው ብለዋል።  አዲሱ ግብር ደግሞ ይላሉ ራይላ ኦዲንጋ ፤ አዲሱ ግብር ደግሞ ይላሉ ሩቶ አሁን "ዛካዮ" የሚል ቅጽል ስም አሰጥቶአቸዋል ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በቅርቡ የዓለም ኤኮኖሚን በተመለከ ባወጣው ዘገባ መሠረት በዓለማችን ፈጣን የኢኮኖሚ  እድገት እያሳዩ ካሉት ሃገራት መካከል ኬንያ፤  አንጎላ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያና ደቡብ አፍሪቃ ናቸዉ ሲል አምስት የአፍሪቃ ሃገራትን ዘርዝሯል።  

የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ሩቶ ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያን 2022 ዓመት፤ መስከረም ወር ላይ የቀድሞዉን የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታን የሰላም ስምምነቱን እንዲከታተሉ ወደ ኢትዮጵያ የሰላም መልዕክተኛ አድርገዉ መላካቸዉ ይታወሳል። ቆየት ብሎ ሕዳር ወር ላይ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ የታጠቂ ቡድኖች ውጥረትን ለማርገብ የክልል ኃላፊነትን ለመወጣት በሚል 900 የኬንያ ወታደሮችን  ወደ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ አሰማርተዋል። ሚያዝያ 2023 ሩቶ፤ በሱዳን በተፋላሚ ወገኖች መካከል ለማደራደር ዝግጁነታቸዉን ቢገልጹም፤ በሱዳን ወታደራዊ መንግስት ዘንድ፤ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱም የሚታወስ ነዉ። ባለፈዉ ነሐሴ ወር 2023 ደግሞ ሩቶ ፤ ኬንያ በሃይቲ የዘራፊ ቡድን ለመከላከል ፖሊሶችን ወደ ሰሜን አሜሪካ ደሰት ወደ ሃይቲ ለመላክ ሐሳብ ማቅረባቸዉ አይዘነጋም።

የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በዩክሬን ያለውን ጦርነት በመቃወም እና ጠንካራ አቋም በመያዝ ለምዕራቡ ዓለም አስተማማኝ አጋር እንደሆኑ ይቆጠራሉ
የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በዩክሬን ያለውን ጦርነት በመቃወም እና ጠንካራ አቋም በመያዝ ለምዕራቡ ዓለም አስተማማኝ አጋር እንደሆኑ ይቆጠራሉምስል Monicah Mwangi/REUTERS

ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ በዩክሬን የሩሲያን ጦር ወረራ አጥብቆ በመቃወም ጠንካራ አቋም መዉሰዳቸዉ ይታወቃል። ሩቶ ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬንን እህል በጥቁር ባሕር እንዲያልፍ ማድረጋቸዉን በግልጽ በመተቸታቸዉ ለምዕራባውያን አገሮች እምነት የሚጣልባቸዉ አጋር ተደርገዉ የሚቆጠሩም ናቸዉ። ይሁንና ይህ አቋማቸዉ ትችት አስነስቶባቸዋል። ኬንያዊዉ የፖለቲካ ተንታኝ ፓትሪክ ጋታራ እንደሚሉት ፕሬዚዳንቱ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ለመሳብ ያደረጉት ጥረት እና አቋም ነዉ ሲሉ ነዉ የተናገሩት። 

«በኬንያ የፖለቲካ ተቃዋሚ መሪ በራይላ ኦዲንጋ እየተነሳ ያለውን ህጋዊነት ጥያቄዎች ለመቅረፍ እና ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን ለመገንባት ብዙ ጥረት እያደረገ ያለ ይመስለኛል»ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የኢትዮጵያው የድርድር ተስፋ

ሩቶ ከአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶችን ለመከላከል ጥረት ማሳየታቸዉ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነዉ።  ባለፈው ሳምንት ናይሮቢ ላይ የተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪቃ የአየር ንብረት ጉባዔ፤ የአየር ንብረት ለዉጥ መንስኤዎችን ለመከላከል የ«ናይሮቢ አዋጅን» በማጽደቅ መጠናቀቁ ይታወቃል።

ከጥቂት ሳምንታቶች በፊት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ይፋ እንዳደረጉት ሃገራቸዉ ኬንያ የሠዉ ልጅ መገኛ በመሆንዋ ማንኛዉም ወደ ሃገሪቱ የሚገባ እንግዳ ቪዛ እንዳያስፈልገዉ እሰራለሁ ብለዋል። ለአሁኑ ከኤርትራ፣ ከጅቡቲ፤ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ከኢንዶኔዢያ ወደ ኬንያ ለጉብኝት የሚገቡ ቪዛ መጠየቅ አያስፈልጋቸዉምም ተብሏል።  

ሩቶ ከአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶችን ለመከላከል ጥረት ማሳየታቸዉ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነዉ።  
ሩቶ ከአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶችን ለመከላከል ጥረት ማሳየታቸዉ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነዉ።  ምስል Khalil Senosi/AP/picture alliance

እንደ ኬንያዊዉ የፖለቲካ ተንታኝ ፓትሪክ፣ የሩቶ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ በዲጂታል እና የኢንተርኔት አጠቃቀም እንዲሻሻል በማድረጉ፤ አገዛዙን ከማረጋጋቱም በላይ የጤና አጠባበቅ ሥርዓትን ለማሻሻል ባለው አጀንዳ እመርታን እያሳየ ነዉ። ከዚህም በላይ የአፍሪቃ የአየር ንብረት ጉባዔን ወደ ሀገሪቱ በማምጣት ስሙን ተክሏል። በናይሮቢ ወጣቶችን በማስተዳደር ሥራ ላይ የተሰራዉ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ኔሪማ ዋኮ እንደሚሉት አስተዳደሩ የፖለቲካ ቁማሩን ትቶ ትኩረቱን ህዝብ ላይ ያድርግ።የኬንያና የኢትዮጵያ ቀጣይ ግንኙነት

«ይህ አስተዳደር የፖለቲካ ቀመርን ያቆመ አይመስልም። በሥራቸው ላይ ከማተኮር ወደ ፖለቲካ ዉስጥ እንደሚገሰግሱ ተስፋ እናደርጋለን።»

በኬንያ አንዳንድ ታዛቢዎች ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አሁን ማድረግ ያለበቸዉ፣ ወደ ስልጣን እንዲመጡ ለእሳቸዉ ድምፅ ለሰጡትና ሕይወታቸው ይሻሻልልናል ብለዉ አምነዉ ከነበሩት ኬንያውያን ጋር እንደገና መገናኘት ይኖርባቸዋል ሲሉ አስተያየታቸዉን ይሰጣሉ።   

አዜብ ታደሰ / ዚሊያ ፍሮሊሽ

ታምራት ዲንሳ