«ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የውህደት ውይይት አልጀመርኩም» ህወሓት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 16 2016ከህዝብ ተደብቆ ከብልፅግና ፓርቲ ጋር የሚደረግ ውህደት የለም ሲል ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ገለፀ። ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመዋሀድ ንግግር ጀመረ ተብሎ መገለፁ ህወሓት አስተባብሏል። ለዶቼቬለ የተናገሩት የህወሓት ከፍተኛ አመራር አቶ እያሱ ተስፋይ ከሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ ብልፅግና ጋር የተጀመረ የውህደት ውይይት የለም ሲሉ የገለፁ ሲሆን የተሰራጨው መረጃም ከእውነት የራቀ ብለውታል።የብልጽግናና የህወሓት ባለሥልጣናት ዉይይት
ለዶቼቬለ የተናገሩት በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ፅሕፈት ቤት የፓርቲው ፕሮፖጋንዳ ዘርፍ ሐላፊ አቶ እያሱ ተስፋይ ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር የሚያገናኘው እና የጋራ አጀንዳው የፕሪቶርያው ውል ነው ያሉ ሲሆን፥ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር አጋዥ በሆኑ ጉዳዮች ብልፅግና ፓርቲ እና ህወሓት በመቐለ እና አዲስአበባ መወያየታቸው ገልፀዋል። የብልጽግና እና የህወሓት ልዩነት እንዴት ከረረ?ከዚህ ውጭ ህወሓት እና ብልፅግና ፓርቲ በመገናኛ ብዙሐን እንደተባለው የጀመሩት ወደ ውህደት የሚመራ ውይይት የለም ሲሉ አስተባብለዋል።ህወሓት እና የሀገሪቱ ገዥ ፓርቲ ብልፅግና መሰረታዊ የዓላማ ልዩነት አላቸው ያሉት የህወሓቱ ከፍተኛ አመራር አቶ እያሱ ተስፋይ ይህ ባለበት አሁን ይሁን ቀጣይ የሚዋሃዱበት ሁኔታ የለም ሲሉ አክለዋል።
"ህወሓት የራሱ ዲስፒሊን ያለው ህዝባዊ ድርጅት ነው፥ ተደብቆ የሚያደርገው ነገር የለም" ያሉት የህወሓቱ አመራር፥ እስካሁን በተደረጉ ግንኙነቶች ውህደት አጀንዳ ያደረገ ውይይት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር እንዳልተደረገ ተናግረዋል።"ከህወሓት ጋር ተደራደሩ ማለት ስህተት ነው" ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
ሌላው ያነጋገርናቸው የሕግ ምሁሩ አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ በበኩላቸው፥ ግጭት ላይ የነበሩት የትግራይ ክልል ገዢ ፓርቲ ህወሓት እና የሀገሪቱ ገዢ ፓርቲ ብልፅግና ወደ ውይይት መመለሳቸው በራሱ ለዘላቂ ሰላም ትልቅ ትርጉም ያለው በማለት ይገልፁታል። እንደ የሕግ ምሁሩ አቶ ሙስጠፋ ገለፃ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚችሉ በርካታ አጀንዳዎች አሉ።
የህወሓት እና ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በያዝነው ወር ሁለት ግዜ በመቐለ እና አዲስአበባ ተገናኝተው ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል። በተነገረው የውህደት አጀንዳ ዙርያ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከብልፅግና ፓርቲ በኩል መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልሰመረም።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ