ጎርፍ ያፈናቀላቸው በጋምቤላ
ሐሙስ፣ መስከረም 21 2013ማስታወቂያ
በጋምቤላ ክልል በጎርፍ የተጎዱ አካባቢ ነዋሪዎች እ|የተሰጠን ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ሲሉ ተናገሩ፣ የክልሉ መንግሥት ለዕለት እርዳታ የሚውል 5 ሚሊዮን ብር መመደቡን የጋምቤላ ክልል መንግሥት አስታውቋል። በክልሉ ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት እየተረባረቡ እንደሆነ ደግሞ የክልሉ አደጋ መከላከል መሥሪያ ቤት አመልክቷል። በክልሉ 30 ሺህ ያህል ህዝብ በጎርፍ ምክንያት መፈናቀልና ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የጋምቤላ ክልል መንግሥት በአፋር በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች አንድ ሚሊዮን 500 ሺህ ብር እርዳታ አድርጓል። ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት ጎርፍ በርካታ ህዝብ ከመኖሪያ ቤቱ የተፈናቀለ ሲሆን ለከፍተኛ የምግብ እርዳታ መጋለጡን የጋምቤላ ክልል አደጋ መከላከል መሥሪያ ቤት አስታውቋል። መሥሪያ ቤቱ ጉዳቱን ከገመገመ በኋላ ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው እርዳታ እየሰጠ እንደሆነ ገልጧል። ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ዝርዝር ዘገባ አለው።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ