ያሻቀበው የዓለማችን የጦር መሣሪያ ግዥና ክምችት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 16 2016ማስታወቂያ
በጎርጎሮሳዊው 2023 በዓለማችን ለጦር መሣሪያ ግዥ የወጣው ገንዘብ ከቀደሙት ዓመታት በ7 በመቶ ማደጉን ዓለም አቀፉ የሰላም ጥናት ተቋም በምህጻሩ SIPPRI አስታውቋል። ተቋሙ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ባወጣው መግለጫ በ2023 ዓ.ም. በዓለማችን ለጦር መሣሪያ ግዥ የወጣው ገንዘብ ወደ 2.43 ትሪልየን ዶላር መጨመሩን አስታውቋል። በእጥፍ የጨመረው የአውሮጳ ሀገራት የጦር መሣሪያ ግዥበስቶክሆልሙ የጥናት ተቋም መግለጫ መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ ቻይና እና ሩስያ ዋነኛዎቹ የጦር መሣሪያ ሻጭ አገራት ናቸው።
የሩስያ ወታደራዊ ወጪ በ24 በመቶ ማለትም በ109 ቢሊዮን ዶላር አድጓል። በዓመቱ የዩክሬን ወታደራዊ ወጪ ደግሞ በ52 በመቶ ማለትም በ65 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ሲል ከተለያዩ ሀገራት ደግሞ ቢያንስ 35 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታም አግኝታለች።
ተቋሙ እንዳለው ዩክሬን ለጦር መሣሪያ ግዥ ያወጣችውና ከውጭ ያገኘችው ወታደራዊ እርዳታ በአጠቃላይ ከሩስያ ወታደራዊ ወጭ 91 በመቶው ያህል ሆኗል።በተቋሙ ጥናት መሠረት በአፍሪቃና በደቡብ አሜሪካ ሀገራትም የጦር መሣሪያ ክምችት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ብሏል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ