1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ውዝግብ ግላዊ ወይስ ድርጅታዊ ?

ሰኞ፣ ግንቦት 10 2012

የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናው ኦፌኮ እና የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ኢሶዴፓ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ኦፌኮ ከመድረክ ጥምረት ባፈነገጠ መልኩ  ሁለት ቦታ እየቆመ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር በየነ ይከሳሉ ። ፕሮፌሰር መረራ በበኩላቸው መንግስት ያቀረበውን አማራጭ እንድንቀበል አጋራቸው ጭምር ግፊት ማድረግ እንደሚፈልጉ አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/3cPFB
Pro Merera Gudina vorsitzender OFECO
ምስል DW/S. Wegayehu

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ) እና የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ውዝግብ

መንግሥት የምርጫ ጊዜን ለማራዘም ለፖለቲካ ፓርቲዎች ባቀረበው አማራጭ ሃሳብ ላይ የመድረክ ተጣማሪ ፓርቲዎች የሆኑት የፕሮፌሰር መረራ ጉዲናው ኦፌኮ እና የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ኢሶዴፓ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ኦፌኮ ከመድረክ ጥምረት ባፈነገጠ መልኩ  ሁለት ቦታ እየቆመ ነው ሲሉ ፕሮፌሰር በየነ ይከሳሉ ። ፕሮፌሰር መረራ በበኩላቸው መንግስት ያቀረበውን አማራጭ እንድንቀበል አጋራቸው ጭምር ግፊት ማድረግ እንደሚፈልጉ አመልክተዋል። የተፈጠረው ልዩነት ከግለሰባዊነት የተሻገረ ድርጅታዊ ምልክታ የለውም ሲሉም መልስ ሰጥተዋል።

Äthiopien Osedepa - Beyene Petros Statement zu aktueller politischer Situation
ምስል DW/G. Tedla

ጌታቸው ተድላ 

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ