1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚ ዐብይ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች

ሰኞ፣ ሐምሌ 16 2010

የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ እስኪ መጣላቸዉ መጠበቅ የለባቸዉም ነበር። ኢህአዴግ ስልጣኑን ለሕዝብ አስረክቦ ሃገሪቱ አዲስ ምርጫን ማካሄድ አለባት። ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ዉይይት ማካሄዳቸዉ በጎ ጅማሮ ነዉ።

https://p.dw.com/p/31xAZ
Äthiopien Premierminister Dr. Abiy diskutiert Reformen
ምስል Prime Minister Office/Fitsum Arega

ኢህአዴግ ሃገሪቱን ለሕዝቡ ማስረከብ አለበት

ኢህአዴግን በምርጫ ለማሸነፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ተደራጅተዉ ጠንክረዉ መዉጣት እንዳለባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መከሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ትናንት እሁድ ከ  200 መቶ የሚበልጡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ተቀብለዉ ዉይይት ባደረጉበት ወቅት ነዉ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቤት ሥራቸዉን እየሰሩ አይደለም፤ በሃገሪቱ የምርጫ ህግ እና ተቋማት ላይ ማሻሻያ ለማምጣት ኢህአዴግ ለሕዝብ ሃገሪቱን ማስረክብ አለበት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስኪጠr4ቸዉ መጠበቅ የለባቸዉም ነበር ሲሉ አንድ የሕግ ባለሞያ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  ዐብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ተቀብለዉ ማነጋገራቸዉ ገንቢ ነበር ተቻችለን ብቻ ሳይሆን አካል ሆነን እንድንሰራ ጥሪ አቅርበዋል ያሉት የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ፕሬዚደንት ተሻለ ሰብሮ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገመንግሥቱ እንዲፈተሽ ወስነዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ እስኪ መጣላቸዉ መጠበቅ የለባቸዉም ሲሉ የተናገሩት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ እንዲያም ሆኖ ጅማሮዉ ጥሩ መሆኑን ገልፀዋል።   

ከስብሰባዉ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መመርያ መሰረት ተሰብሳቢዎች በሙሉ የኢትዮጵያ የመረጃና የደሕንነት መስርያ ቤትን ጎብኘተናል፤ አዳዲሶቹን ሹማምንቶች ሁሉ ተዋዉቀናል በዚህም በመካከላችን የነበረዉ ጥቁር መጋረጃ ተቀድዋል ያሉት የኢራፓ ፓርቲ ፕሬዚዳንት፤ በስብሰባዉ ላይ የሕገ መንግሥት መሻሻል ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ጉዳይ አንዱ ነበር።    

ኢህአዴግ ነጻና ገለልተኛ ተቋም ማቋቋም አቅም የለዉም ያሉት የሕግ ባለሞያዉ አቶ ተማም አባቡልጉ፤ በአሁኑ ወቅት ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ከሰንደቃላማ ይበልጥ ብዙ ሊሰሩ የሚገባቸዉ ነገሮች አሉ፤ ይህ የሚያመለክተዉ ፓርቲዎቹ አጀንዳ ማጣታቸዉን ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

አዜብ ታደሰ  

ነጋሽ መሐመድ