የጎርፍ አደጋና ስጋት በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ነሐሴ 14 2013ማስታወቂያ
የዘንድሮዉ ክረምት ዝናብ ኢትዮጵያ ዉስጥም የሰዉ ሕይወት፣ ሐብትና ንብረት እያጠፋ ነዉ።ግራ አጋቢዉ የዝናቡ ማየል አይደለም።አንዳድ ቀን ፀኃዩ ገርሮ ነዋሪዉን ሲያማርር ይዉልና በማግስቱ ወይም በሌለኛዉ ቀን በረዶ የቀላቀለ ከባድ ነጎድጓዳማ ዝናብ ባካባቢዉን ይወርዳል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚትርዮሎጂ ኤጄንሲ እንደሚለዉ ደግሞ ከባዱ ዝናብ እስካሁን ካደረሰዉ ጉዳት በላይ ሊያደርስ ይችላል።የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ጫሊ ደበሌ ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት በእስካሁኑ ዝናብ ወንዞችና ኮሬዎች እየሞሉ፣መሬቱን እየረጠበ በመሆኑ ተጨማሪ ዝናብ ሲጥል አደገኛ ጎርፍ ማስከተሉ አይቀርም።
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ