1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት መንግስት ምን እያደረገ ይሆን ?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 9 2016

በኢትዮጵያ የተወሰደውን የኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ የዋጋ ችማሪ ወደፊት ያጋትማል በሚል በምርት ስወራ እና “ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ላይ የተሰማሩት” ከ39 ሺህ 500 በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ የተለያዩ እርመምጃዎች መውሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

https://p.dw.com/p/4jWcG
Äthiopien Alltag l Dire Daw Market
ምስል Mesay Teklz/DW

በህገ ወጥ ተግባራት በተሰማሩት ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው ፤ ንግድ ሚኒስቴር

ስለዋጋ አለመረጋጋትና እልባቱ የንግድና ቀጣናዊ ሚኒስቴር አስተያየት

በኢትዮጵያ የተወሰደውን የኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ የዋጋ ችማሪ ወደፊት ያጋትማል በሚል በምርት ስወራ እና “ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ላይ የተሰማሩት” ከ39 ሺህ 500 በላይ የንግድ ድርጅቶች ላይ የተለያዩ እርመምጃዎች መውሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለስልጣን ከገቢያው አለመረጋጋት በኋላ ተደርጓል ባሉት ክትትልና ቁጥጥር የምርት አቅርቦት እጥረት ሳያጋጥም ምርትን በመደበቅ የመሰማራት ተግባር በነጋዴው ማህበረሰብ ዘንድ ጎልቶ ታይቷልም ነው ያሉት፡፡

ትግራይ ከኤኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ እንደንምን ሰነበተች ?

አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ አልቃድር ኢብራሂም፤ አገራዊውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ የተፈጠረውን የዋጋ አለመረጋጋት ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሎች የንግድ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የጋራ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስረድተዋል፡፡ “ኮሚቴው ብሔራዊ የንግድ ተቋማት የጸረ-ህገወጥ ንግድና ገቢያ መቆጣጠሪያ ኮሚቴ” እንደሚሰኝ የገለጹት ኃላፊው፤ ኮሚቴው እስከታኛውን እርከን መዋቅር የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በምርት ስወራና ዋጋ ጭማሪ ላይ ፈጸማል ያሉትን ተግባር እንደሚቆጣጠር ገልጸዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ መጋዘን ዉስጥ የተከማቸ ዘይት
አገራዊውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ የተፈጠረውን የዋጋ አለመረጋጋት ተከትሎ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልሎች የንግድ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የጋራ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስረድተዋል፡፡ምስል Mesay Teklz/DW

የምጣኔ ሃብት ማሻሻያው በአማራ ክልል ግብይት ላይ ምን አስከተለ?

እንደመንግስት ከዚህ በፊት ወደ አገር ገብተው በነጋዴዎች እጅ ላይ የሚገኙ ምርቶችን በጭማሪ ዋጋ የመሸት ምንም አይነት አግባብነት እንደሌለም ነው ሚታመነው ብለዋል፡፡ እየተደረገ ያለውም ቁጥጥርና ክትትል ይህንኑን መሰረት በማድረግ ነው ያሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃልአቀባይ ምናልባት ወደፊት የሚገቡ ምርቶች ላይ ሁኔታውና አግባብነቱ ታይቶ ጭማሪ ማድረግ ብቻ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የተለያዩ እርምጃዎች የተወሰደባቸው የንግድ ተቋማት

 የህግ አግባብን በመጣስ ገቢያው እንዳይረጋጋ ተሳትፎን አድርገዋል የተባሉ ከ39 ሺህ 500 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ተቋማቱን የማሸግና የእስር እርምጃዎች መወሰዱንም ኃላፊው አክለው አብራርተዋል፡፡ “ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ብሎም የንግድ ፍቃዳቸውን ከማሸግ እስከ ፈቃዳቸው መሰረዝ፤ ብሎም ከበድ ያለ ጥፋት አጥፍተው በተገኙት ላይ ደግሞ የእስራት እርምጃ ሁሉ እተወሰደ ይገኛል፡፡ እስከ ነሃሴ 07 ብቻ ከ39 ሺህ 564 የንግድ ተቋማት ላይ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስዷል” ነው ያሉት፡፡

የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ሱቅ
 የህግ አግባብን በመጣስ ገቢያው እንዳይረጋጋ ተሳትፎን አድርገዋል የተባሉ ከ39 ሺህ 500 በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ከጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ ተቋማቱን የማሸግና የእስር እርምጃዎች መወሰዱንም ኃላፊው አክለው አብራርተዋል፡፡ ምስል Mesay Teklz/DW

በአዲስ አበባ ከተማ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን የተከተለው የገበያ አለመረጋጋት

ከቁጥጥር ባሻገር ስለአቅርቦት ምን ታስቧል?

መሰል የቅጣት እርምጃዎች ብቻ ገቢውን ልያረጋጉት ይችላሉ ወይ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና የኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ አልቃድር ኢብራሂም፤ “በምንግስት በኩል ቀደም ብለው የሚገቡ እንደ ዘይት እና ስኳር እንዲሁም ከዚህ ቀደም በፍራንኮ ባሎታ የተፈቀዱ ሸቀጦች በመደበኛው ሁኔታ እየገቡና ለሸማቹ እቀረቡ ብሆንም የምርት አቅርቦት እጥረት ችግር ባልሆነና የነጋዴዎች የምርት ስወራ ምክንያት ብቻ እጥረቱ ተፈጥሯል” ሲሉ አመልክተዋል፡፡

አምራቾችም ምርት በተጠናከረ መልኩ እንዲያመርቱ ብሎም የምርት ስወራ ክትትልና ቁጥጥር ላይ እርምጃ መውሰድ በቀጣይነት የተቀመጠ አቅጣ መሆኑንም ነው ያመለከቱት፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ