የጆ ባይደን የአውሮጳ ጉብኝት
ሐሙስ፣ ሰኔ 10 2013ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአንድ ሳምንት የአውሮጳ ጉብኝታቸው አጠናቀው ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል። ባይደን በአውሮጳ ቆይታቸው ብሪታንያ ባስተናገደችው ቡድን ሰባት በሚባሉት ባለፀጋ ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ፣ በሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል። ከአውሮጳ ኅብረት ባለሥልጣናትም ጋር ተወያይተዋል። ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋርም ትናንት ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ውስጥ ውጤታማ የተባለ አካሂደዋል። ስለ ባይደን የአውሮጳ ጉዞ ውጤትና አንድምታው የብራሰልሱን ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ