1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ገንዘብ ሚንስትር ተባረሩ፣ ተጣማሪዉ መንግሥት ፈረሰ

ነጋሽ መሐመድ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 28 2017

የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ የሐገሪቱ የገንዘብ ሚንስትርና የነፃ ዴሞክራቶች ፓርቲ (FDP) መሪ ክርስቲያን ሊንድነርን ትናንት ከሥልጣን በማባረራቸዉ የሀገሪቱ ተጣማሪ መንግሥት ፈርሷል። ሾልስ የገንዘብ ሚንስትሩን ከሥልጣን ያባረሩት ሚንስትሩ የተጣማሪ መንግሥቱን የጥምረት ዉል የሚፃረር የምጣኔ ሐብት መርኅ በማቅረባቸዉ ነዉ።

https://p.dw.com/p/4mkhY
Deutschland Berlin 2024 | Bundestag stimmt über Antrag zu jüdischem Leben in Deutschland ab
ምስል Political-Moments/IMAGO

የጀርመን ጥምር መንግሥት ምሥረታ ጥረት ፈረሰ

የጀርመን መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ የሐገሪቱ የገንዘብ ሚንስትርና (FDP) በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉን የነፃ ዴሞክራቶች ፓርቲ መሪን ክርስቲያን ሊንድነርን ትናንት ከሥልጣን በማባረራቸዉ የሀገሪቱ ተጣማሪ መንግሥት ፈርሷል ። ሾልስ የገንዘብ ሚንስትሩን ከሥልጣን ያባረሩት ሚንስትሩ የተጣማሪ መንግሥቱን የጥምረት ዉል የሚፃረር የምጣኔ ሐብት መርኅ በማቅረባቸዉ ነዉ።

የጀርመን ምክር ቤት (Bundestag)  በመጪዉ ጥር ለቀሪዉ የሾልስ መንግሥት የመታመኛ ድምፅ እንዲሰጥ ሾልስ ጠይቀዋል። በመጪዉ መጋቢት ምርጫ ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል። ሥለ ጀርመን ተጣማሪ መንግስት መፍረስ ነጋሽ መሐመድ በርሊን የሚኖሩትን የፖለቲካ ተንታኝና የፈደራል ጀርመን ታላቅ የመስቀል ሜዳይ ተሸላሚ ዶክተር ፀጋዬ ደግነሕን በሥልክ አነጋግሯቸዋል።

በዛክሰን አንሀልትና ቱሪንገን በተባሉት በምሥራቅ ጀርመኖቹ ግዛቶች ከሁለት ወራት ግድም በፊት በተካሄደው አካባቢያዊ ምርጫ ፣ የጀርመን ጥምር መንግሥት አባላት የሆኑት ሦስት ፓርቲዎች ጉድ ሆነዋል። በነዚህ ፌደራዊ ግዛቶች ቀኝ ጽንፈኛው አማራጭ ለጀርመን ፓርቲ ከሦስቱ ፓርቲዎች ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ድምፅ ማግኘቱ አስደንግጧቸዋል ። ያም ብቻ አይደለም ሦስቱ ዋነኛ ፓርቲዎች በጋራ ጥምር መንግሥት ለመመስረት ያደረጉት ጥረት መክሸፉ ዛሬ ይፋ ሁኗል ። ቀጣዩ ምን ይሆን? 

ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከድምጽ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል ።

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ