1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኔስኮ የምሥጋና ዝግጅት ለአፍሪቃውያን የ«ቱር ደ ፍራንስ» ተወዳዳሪዎች

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 21 2007

ለሶስት ሳምንታት ሲካሄድ ሰንብቶ ባለፈው እሁድ በተጠናቀቀው የ«ቱር ደ ፍራንስ» የቢስኪሌት እሽቅድድም ውድድር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ «ኤም ቲ ኤን ኩቤካ» የተባለ አንድ የአፍሪቃ ቡድን ተካፋይ መሆኑ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/1G6Wx
Frankreich Tour de France 2015 8. Etappe
ምስል Getty Images/D. Pensinger

[No title]

መንበሩን ደቡብ አፍሪቃ ባደረገው በዚሁ ቡድን ውስጥ አባል ከሆኑት መካከል ኤርትራውያን እና ደቡብ አፍሪቃውያን ተወዳዳሪዎች በዚሁ የመጀመሪያ ተሳትፏቸው ያስመዘገቡት ውጤት የሚበረታታ እንደነበር ተገልጾዋል። የተመ የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት፣ ዩኔስኮ እና የድርጅቱ ቋሚ የአፍሪቃ መልዕክተኞች 102 ዓመታት በሆነው የቱር ደ ፍራንስ ውድድር ላይ አፍሪቃን ለወከለው ለዚሁ ለ«ኤም ቲ ኤን ኩቤካ» ቡድን በፓሪስ ጽሕፈት ቤቱ አንድ ልዩ የምሥጋና ዝግጅት አካሂደዋል።

ሀይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ