1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዑ ልዑክ ማይክ ሐመር መግለጫ

ዓርብ፣ መስከረም 3 2017

ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር የሰሞኑ ጉዟቸው አላማ ኢትዮጵያ ውስጥ በየክልሎች የሚካሄደውን ግጭት ለማስቆም ውይይት ማድረግ እና በትግራይ ክልል የጠመንጃ ላንቃ መዘጋቱን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/4kbzv
ማይክ ሃመር
ማይክ ሃመር ምስል Seyoum Getu/DW

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዑ ልዑክ ማይክ ሐመር መግለጫ

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዑ ልዑክ ማይክ ሐመር መግለጫ

ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር የሰሞኑ ጉዟቸው አላማ ኢትዮጵያ ውስጥ በየክልሎች የሚካሄደውን ግጭት ለማስቆም ውይይት ማድረግ እና በትግራይ ክልል  የጠመንጃ ላንቃ መዘጋቱን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን ገልፀዋል። ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትን እና ሕብረት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነች ያሉት ባለሥልጣኑ፣ ይህ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት አንኳር ጉዳይ ነው ብለዋል። በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ጨምሮ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መሪዎችን እና የሕወሓት ኃላፊዎችን ትግራይ ውስጥ ማግኘታቸውን ሆኖም በቀጠለው ግጭት ምክንያት ወደ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች መጓዝአለመቻላቸውን ተናግረዋል። 

ከኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት እና ከሕወሓት መሪዎች ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን የገለፁት የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር በፕሪቴሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ዙሪያ በተለይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ እና ከኅብረተሰቡ ጋር መቀላቀል የሚሉ ጉዳዬች ላይ መምከራቸውን እና ሁለት ዓመት የሞላው ስምምነት አፈፃፀሙ በአፋጣኝ ተግባራዊ መሆን በሚችልበት ጉዳይ ላይ ማተኮራቸውን ገልፀዋል። በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ከመከላከያ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኅልይሎች በተለይ የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ክልል እንዱወጡ የሚለው ነጥብ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን ጉዳዩን ከሚመለከተው የአፍሪካ ሕብረት ሰዎች መስማታቸውንም ጠቅሰዋል።

ሀገራቸው ዩናይት ስቴትስ በኢትዮጵያ በፊት ለይ በአማራ ያለው ግጭት እንደሚያሳስባት የገለፁት ሐመር በኢትዮጵያ የUS ኤምባሲ የክልሉን ጉዳይ በቅርበት ይከታተላል ብለዋል። በቀጠለው ግጭት ምክንያት ወደ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ለመጓዝ አለመቻላቸውን ሆኖም ውይይት መደረግ እንዳለበት ይህም ከካሜራ እይታ ውጪ ሊሆን እንደሚገባም በመግለጫቸው ገልፀዋል። "ወደ ኢትዮጵያ ባደረግዃቸው ጉዞዎች ሁሉ ትኩረቴ ፥ አምባሳደር ማሲንጋ በግንቦት 15 ንግግራቸው ላይ እንደገለፁት በመላው ኢትዮጵያ - በአማራም ሆነ በኦሮሚያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም ውይይት ማድረግ እና በእርግጥም እንደ እድል ሆኖ በትግራይ የጠመንጃ ላንቃ መዘጋቱን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ማስቀጠል ነው"።  

በትግራይ ክልል በነበራቸው ጊዜ ከመቀሌ ከተማ ውጪ ያለ የመጠለያ ጣቢያ መጎብኘታቸውን፣ ተፈናቃዮች ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ መመልከታቸውንና ሀገራቸው ድጋፍ ማድረግ እንደምትቀጥል፣ ተፈናቃዮችም ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በሁለቱም ወገን ላይ ግፊት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል። "...በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ሁሉ በሰላም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ በትኩረት ሁሉም የስምምነቱ አካላት ሙሉ በሙሉ መተግበራቸውን ለማረጋገጥ፣ በእርግጥ የትጥቅ ማውረድ፣ የማስፈታት እና መልሶ የመዋሃድ መርሃ ግብሮችን ማረጋገጥ እና ዋና ዋና ጉዳዮችን በፖለቲካ ውይይት መፍታት የሚለውን ማረጋገጥ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትን እና ሕብረቷን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነች። ይህ ከኢትዮጵያ ጋር ያለን አጋርነት አንኳር ጉዳይ ነው"። 

እዚህ በመጡ ጊዜ ሁሉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሀገሪቱ ሰላም ጉዳይ ዙሪያ እንደሚነጋገሩ ያስታወቁት ማይክ ሐመር የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት በትክክል እንዲተገበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እና የሕወሓት ኃላፊዎች ሙሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውንና ያንንም እንዳረጋገጡላቸው አስታውቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስም ለዚህም ሙሉ ቁርጠኝለት እንዳት ተናግረዋል። በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ጦርነት ሊኖር እንደማይገባ እና የሁለቱ ሀገራት የግዛት ወሰን መከበር እንዳለበት በውይይታቸው ወቅት መንሳታቸውንም አመልክተዋል። ሐመር አሜሪካ የሶማሊያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት ታከብራለችም ብለዋል። ከአሜሪካ አንፃር ኢትዮጵያ በሶማሊያ የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመግታት የምታደርገውን መስዋእትነት ያስታወሱት ኃላፊው እንዴት ያንን ማስቀጠል አለብን የሚለው ላይ የሚያትኩሩ ስለመሆኑም በመግለጫቸው ገልፀዋል።

 

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ