ሐሙስ፣ ግንቦት 8 2016-ፑቲን፤ ቻይና በዩክሬን ውስጥ ላለው ጦርነት መፍትሄ ለማፈላለግ ስለመሞከርዋ አመሰገኑ። ፑቲን ይህ የተናገሩት ለሁለት ቀናት ጉብኝት መዲና ቤጂንግ ዛሬ ማለዳ ከገቡ በኋላ ነዉ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የታሰሩበትን ሊቀመንበ ጨምሮ የኅሊና እስረኞች ያላቸው ሌሎች ታሳሪዎች ሁሉ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ይፈቱ ሲል ጠየቀ።
በኢትዮጵያ ሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ጥላ ሥር የሚገኙ፤ 367 ሲቪል ድርጅቶች፤ ሕገ መንግሥት እና ሕገ መንግስታዊነት ብሎም የሀብት እና የሥልጣን ክፍፍል፤ ዋነኛ የሀገራዊ ምክክር ጉዳዮች እንዲሆኑ ጠየቁ።