1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወባ በሽታ ስርጭት በምዕራብ ወለጋ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 7 2016

የአሶሳዉ ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ያነጋገራቸዉ ነዋሪዎች ግን የኬሚካል ርጭቱ ወባ በስፋት በሚገኝባቸው ቀበሌዎች ባለመዳረሱና በቂ መድሃኒት ባለመሆኖሩ በሽታዉ አሁንም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4XheQ
የተለያዩ የወባ መከላከያ ክትባቶች
የወባ መከላከያ ክktትባትምስል Joseph Oduor/AP Photo/picture alliance

ምዕራብ ወለጋ የወባ በሽታ ስርጭት በመጠኑ ቀንሷል

 

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቆንዳላ ወረዳ ውስጥ የጸረ ወባ ኬሚካል በመረጨቱ በወረዳው 9 ቀበሌዎች ውስጥ ተዛምቶ የነበረዉ የወባ በሽታ መቀነሱን የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ገልጸዋል፡፡ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ዮሰፍ ባርከሳ በወረዳው 16 ቀበሌዎች ውስጥ የወባ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የአሶሳዉ ወኪላችን ነጋሳ ደሳለኝ ያነጋገራቸዉ ነዋሪዎች ግን የኬሚካል ርጭቱ ወባ በስፋት በሚገኝባቸው ቀበሌዎች ባለመዳረሱና በቂ መድሃኒት ባለመሆኖሩ በሽታዉ አሁንም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ቆንዳላ ወረዳ የጤና ባለሙያ መሆናቸውን የነገሩን አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ የወባ በሽታ ስርጭት በወረዳው አሁንም እየጨመረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ በቅርብ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር በሰባት ተሽከርካሪዎች የኬሚካልና የተለያዩ ቁሳቀሶችን ለቆንዳ ወረዳ እና ቤጊ ወረዳ መላካቸውን ነዋሪው ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም በወረዳው በተለያዩ ምክንያቶች የወባ በሽታ ቅድመ መከላከል ስራ አነስተኛ ስለነበርና በአካባቢው የምግብ እጥረት በመኖሩ ስርጭቱ በዚህ መስከረም ወርም መጨመሩን አመልክተዋል፡፡ የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭት ቤት ለቤትና ውሃ ባቆሩ ስፍራዎች ሙሉ በመሉ ባለመሰራቱ አሁንም ወባ በአካባቢው በወረርሽኝ መልክ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ወባን ለመከላከልና ለማጥፋት በየጊዜዉ ቢታቀድም እስካሁን ኢትዮጵያ ዉስጥ በሽታዉ ብዙ ሰዎች እየጎዳ ነዉ።
ወባን ለማጥፋት በሚቻልበት ስልት ላይ የተነጋገረ ስብሰባ-አዳማምስል Seyoum Getu/DW

በወረዳው በግል ስራ ተሰማርቶ እንደሚገኙ እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላው ባለሞያም በወረዳው በአብዛኛው አካባቢዎች የጸረ ወባ ኬሚካል ርጭት አለመዳረሱን ገልጸዋል፡፡ ህብረተሰሆቡ በቂ መድሃኒት እያገኘ እንዳልነም ተናግረዋል፡፡ አሹንፋ በተባለ ቦታ ባለፈው አርብ  2 ሰው ህይወት ማለፉንአመልክተዋል፡፡
‹‹ ገሚ ጋባ፣ሹራ ማራሞ የተባሉ ቀበሌዎችን ጨምሮ ባጠቃላይ በአራት ቀበሌዎች ውስጥ የኬሚካል ርጭት መከናወኑን አይተናል፡፡ ሆኖም የወባ ስርጭትን ለመከላከል አሁንም ትኩረት ይፈልጋል፡፡ በሰው ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት አልቀነሰም፡፡ የመድሀኒትና የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡‹‹

የቆንዳላ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዩሰፍ ባርከሳ በወረዳው ስር ከሚገኙት 32 ከሚደርሱት ቀበሌዎች መካከል በ16ቱ የኬሚካል ርጭት መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ በወረዳው አገልግሎት ከሚሰጡት አራት የጤና ተቋማት ውስጥ በአንዱ ጤና ጣቢያ  ለሳምንት ያህል ታመው  ወደ ተቋሙ በሚመጡ ሰዎች ላይ ወባ አለመታየቱን ገልጸዋል፡፡ 3ቱ ጤና ጣቢዎች በሚገኙባቸው ስፍራዎች ደግሞ የወባ በሽታ በወረርሽኝ መልክ መታየቱ ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው ባለፉት 3 ዓመታት በጸጥታ ችግርና ልዩ ልዩ ምክንያት የወባ መከላከያ አጎበር ለህብረተሰቡ አለመሰራጨቱን አክለዋል፡፡ 
‹‹ ባለፈው 1 ወር  ከ3 ሳምንት ውስጥ 5939 ሰዎች ታመው ወደ ጤና ጣቢያ  ከመጡት መካከል  4322 ሰው ላይ የወባ በሽታ ታይቷል፡፡ እስካሁን በጤና ጣቢያ ተመርመረው  5 ሰዎች በወባ በሽታ ታመው ህይወታቸው አልፈዋል፡፡ ወባን ለመከላከል የኬሚካል ርጭት ቤት ለቤት በተወሰነ መልኩ ተሰርቷል፡፡  ጋባ ዳፍኖ የተባለ አካባቢ ወባ በወረርሽ መልክ እንቀጠለ ነው፡፡  ‹‹
በሐምሌ እና ነሐሴ 2015 ዓ.ም ለቆንዳላ እና አካባቢው አገልግሎት በሚሰጠው የቤጊ ሆስፒታል ውስጥ 29 ሰዎች ህይወት በወባ በሽታ ምክንያት ማለፉን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በ117 ወረዳዎች ወባ በወረርሽኝ መልክ መታየቱን ከዚህ ቀደም የክልሉ ጤና ቢሮው አመልክተዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ እና ቀሌም ወለጋ ዞኖች ወባ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱም ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

ከወባ መከላከያ ዘዴዎች አንዱ
ሕንዶች የወባ ስርጭትን ለመከላከል ከሚጠቀሙበት ስልት አንዱምስል Naveen Sharma/SOPA/ZUMA/picture alliance

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በምዕራብ ወለጋ ቤጊ ወረዳ በረሀብና በወባ ወረርሽኝ የሰው ህይወት ማለፉን መረጃ እንደደረሰው ይፋ አድርጓል፡፡ በአራቱም የወለጋ ዞኖች በጸጥታ ችግር ምክንያት አርሶ አደሩ በተገቢው ሁኔታ ወደ እርሻ አለመግባቱንና ለግብርና ግብአት የሚሆኑ አቅርቦት አለማግኘቱን በመግለጫው አክለዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ