የኢትዮጵያዉያን የፍልሰት አዙሪት
ሐሙስ፣ ጥር 26 2014«አሁን ስንመለከተዉ፤ ፍልሰት እንደባህል እየሆነ ነዉ። ወጣቶች በተለይ ከወጣትነት ወደ ጎልማሳነት የሚሸጋገሩ ዜጎች ወደሌሎች ሃገሮች መሄድ እና አዲስ ነገር ማግኘትን የሚሹ ናቸዉ። የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃንም ትልቅ ሚናን ይጫወታል» በፍልሰት ላይ የተለያዩ ጥናቶች ያካሄዱት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት አስናቀ ከፍአለ ናቸዉ።
የመኖርያ ፈቃድ የላችሁም ተብለዉ በሳዉዲ አረብያ በሚገኙ እስር ቤቶች ከ 50 እስከ 70 ሺህ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እየማቀቁ እንደሆን የነገረን ደግሞ በሳዉዲ ማንነቱ እንዲነገር የማይፈልግ ኢትዮጵያዊ ነዉ። ለብዙ ወራቶች ሳዉዲ ዉስጥ በሚገኙ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ዜጎች እንዲደርሱላቸዉ ጥሪ እያቀረቡ መሆኑን የሚያሳይ በፎቶ የተደገፈ ብሎም ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይታያል። ባለፈዉ ሰሞን ወደ ሳዑድ አረብያ የተጓዘዉ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑካን ቡድን በሳዉዲ ቆይታዉ ከፈጸማቸዉ ነገሮች መካከል እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አያያዝ ስለሚሻሻልባቸው፣ የመኖሪያ ፈቃዳቸው የተቃጠለና የተለያዩ ቅጣቶች የሚጠብቋቸው ነገር ግን በራሳቸው ገንዘብ ተሳፍረው አገራቸው መግባት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ቅጣት ተነስቶላቸውና ምህረት ተደርጎላቸው ወደ ሀገራቸው መመለስ በሚችሉባቸው አግባቦች ላይ ተስፋ ሰጭ ዉይይት ተደጎአል ተብሎአል። ኢትዮጵያን ሃገራቸዉን ለቀዉ ወደ ሌሎች ሃገራት መሰደዳቸዉ ከዓመት ዓመት እንደጨመረ የነገሩን በፍልሰት ጉዳይ ላይ የተለያዩ ጥናቶችን ይፋ ያደረጉት ተባባሪ ፕሮፌሰር አስናቀ ከፍአለ እንደሚሉት፤ ስደት ከሚለዉ ይለቅ ፍልሰት የሚለዉ ቃል የተሻለ መሆኑን ይናገራሉ። ፍልሰት ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ባህላዊ የመሳሰሉ የተለያዩ አይነቶች እንዳሉትም ይናገራሉ። እንደ ዶክተር አስናቀ ከመላዉ አፍሪቃ ሃገራት የኢትዮጵያን ፍልሰት መጠን በአማካኝ አነስተኛ ነዉ።
ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ የሚደረግ ፍልሰት የተጀመረዉ በ70ዎቹ በሃይማኖት ምክንያት ለሃጂና ኡምራ ጉዞ ሲደረግ ነዉ። ከዝያም የኢህአዴግ መንግሥት ከገባ በኋላ ነዉ ሲሉ በስደት ጉዳይ ላይ ጥናት የሚያካሂዱት ተባባሪ ፕሮፌሰር አስናቀ ከፍአለ ተናግረዋል። በስደት ላይ የምናጠና ሰዎች ከኢትዮጵያ ቪዛ እያገኙ በሕገ የሚጓዙ ሰዎች ሕገ-ወጥ ስደተኞች ሳይሆን ኢ-መደበኛ ስደተኞች ነዉ የምንላቸዉ ሲሉም ተናግረዋል።
ሳዉዲ ዉስጥ ሃበሻ በተለየ ሁኔታ ነዉ እየተፈለገ የሚታሰረዉ ያለን ስሙን መግለጽ ያልፈለገዉ የሳዑዲ አረብያ ነዋሪ የመኖርያ ፈቃድ የሌለዉ ሕገ-ወጥ ስደተኛ በጥቆማ ሁሉ ነዉ የሚያዘዉ። በሳዑዲ አረብያ ሁኔታዉ ከባድ እየሆነ እየታወቀ ዜጎች ለምን ወደዝያ ይጓዛሉ የሚለዉ ጥያቄን ዉስብስብ ነዉ ያሉት ተባባሪ ፕሮፌሰር አስናቀ ከፍአለ፤ በስድት ጉዳይ ላይ የሚያጠኑ ምሁራን እንዳሉት ሳቢና፤ ሰዎች የሁኔታን አለመመቸት እያዩም ቢሆን የሚሰደዱት ሳቢና ገፊ ነገሮች በመኖራቸዉ ነዉ።
ከኢትዮጵያ ወደ ሳዉዲ አረብያ የሚጓዙት ኢመደበኛ ነዉ የሚባሉት? በሳዉዲ አረብያ ብቻ ምን ያህል ስደተኞች አሉ ተብሎ ይገመታል? በሳዉዲ እስርቤት ጥቁር ላስቲክ ለብሰዉ የሚታዩት ኢትዮጵያዉያን፤ ለበርካታ ወራቶች ልብስ ቀይረዉ ስለማያዉቁ ያን ተከትሎ ከሚመጣ ተባይ ምክንያት ነዉ ሲል ከሳዉዲ አረብያ መረጃ የሰጠን ልጅ አክሎ ተናግሮአል።
የሚፈልሱት ገንዘብ ያላቸዉ ሰዎች ናቸዉ። ምክንያታቸዉ ደግሞ የተሻለ የስራ እድል ልዩ ጥቅማጥቅም እና የኑሮ ሁኔታ በተለይ ወደ ምዕራብ አዉሮጳ የሚጓዙ የማኅበራዊ ጥበቃ ድጋፍም መኖሩንም ነዉ ሲሉ ዶክተር አስናቀ ከፍአለ ተናግረዋል። አሁን አሁን ደግሞ ፍልሰት ባህል እየሆነ መጥቶአል ባይ ናቸዉ። በትዉዉቅ ወደ ሌላ ሃገር መጓዝ ሌላዉ የፍልሰት መንገድ ነዉ ያሉት ፍልሰት ተባባሪ ፕሮፌሰር አስናቀ ከፍአለ፤ ሰዎች ወደ አደገኛዉን መንገድ እንዳይጀምሩ ግን ማስቆም አይቻልም ፤ ይቀጥላል።
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ