1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና ቻይና ትብብር አዲስ ምእራፍ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 2016

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ ከቻይናው መሪ ሺ ጂንፒንግ ጋ ቤጂንግ ውስጥ ዛሬ ስለሁለቱ ሃገራት ላቅ ያለ ትብብር መነጋገራቸውን ከቻይና የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል ። ቻይና እና ኢትዮጵያ «ዘላቂ የሆነ ሥልታዊ ትብብር» የሚል ስያሜ የተሰጠው ስምምነት ማድረጋቸውም ተጠቅሷል ።

https://p.dw.com/p/4XeKj
«ቀበቶ እና መንገድ ተነሳሽነት» (BRI) በተሰኘው የቻይናው ግዙፍ ፕሮጄክት ሦስተኛ ጉባኤ ላይ ተሳታፊዎች
«ቀበቶ እና መንገድ ተነሳሽነት» (BRI) በተሰኘው የቻይናው ግዙፍ ፕሮጄክት ሦስተኛ ጉባኤ ላይ ተሳታፊዎች ለፎቶ ተደርድረው ። ቤጂንግ፤ ቻይና፤ ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ምስል Sergey Savostyanov/ASSOCIATED PRESS/picture alliance

«ዘላቂ የሆነ ሥልታዊ ትብብር» ቻይና፥ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ ከቻይናው መሪ ሺ ጂንፒንግ ጋ ቤጂንግ ውስጥ ዛሬ ስለሁለቱ ሃገራት ላቅ ያለ ትብብር መነጋገራቸውን ከቻይና የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ቻይናየሚገኙት «ቀበቶ እና መንገድ ተነሳሽነት» (BRI) በተሰኘው የቻይናው ግዙፍ የግንባታ ፕሮጄክት ሦስተኛ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ  መሆኑም ተዘግቧል ። የቻይና መንግሥት ዜና አገልግሎት «ዢኑዋ» ዛሬ እንዳተተው ከሆነ፦ ቻይና እና ኢትዮጵያ «ዘላቂ የሆነ ሥልታዊ ትብብር» የሚል ስያሜ የተሰጠው ስምምነት ማድረጋቸውም ተጠቅሷል ።

ሩስያ እና ቻይናን ጨምሮ አምስት ሃገራት ያቋቋሙት የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር በእንግሊዥኛው (BRICS) ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሃገራትን ከጎርጎሪዮሱ አዲስ ዓመት ጀምሮ በሙሉ አባነት እንደሚቀበል ቀደም ሲል መገለጹ የሚታወስ ነው ። የሩስያው ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን 130 ሃገራት ይታደሙበታል በተባለው የቻይናው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ቤጂንግ መግባታቸው ተገልጿል ። 

ዶክተር አደም ካሴ ዘ ሔግ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲ እና የምርጫ ሥርዓት ድጋፍ ሰጪ ተቋም (IDEA) ከፍተኛ አማካሪ ናቸው ። በቻይናና ኢትዮጵያመካከል «ዘላቂ የሆነ ሥልታዊ ትብብር» በሚል ተደረገ የተባለው ስምምነት ምን ማለት ነው የሚለውን በማብራራት ይጀምራሉ ። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ