የኢትዮያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ እራሱን ከመድረክ አገለለ
ሐሙስ፣ ጥር 20 2013ማስታወቂያ
በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እራሱን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በማግለል በቀጣዩ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ በተናጠል እንደሚወዳደር ዐስታወቀ። የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለዶይቼ ቬለ እንዳረጋገጡት በተለይም ለፓርቲያቸው ከመድረክ ለመውጣት መወሰን ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጋር እየተፈጠረ የመጣው ልዩነት ዋነኛው ምክኒያት ነው።
የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው እንዳረጋገጡት ኢሶዴፓ በራሱ ፈቃድ ከመድረክ እየተገለለ መምጣቱ እውን ቢሆንም ፊቺው ግን ገና በይፋ በጠቅላላ ጉባኤ ያልተደመደመ ነው ብለዋል። ኦፌኮ በመድረክ ስር በተለመደው ሁኔታ ይቀጥላል ያሉት አቶ ሙላቱ የተለያዩ ፓርቲዎች መድረክን በጥምረት ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡም ይገኛሉ ነው ያሉት።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ