የኢትዮ-አሜሪካ ዲፕሎማሲ መሻከር አንድምታ
ዓርብ፣ ግንቦት 27 2013ማስታወቂያ
በአሜሪካ እና ኢትዮጵያ መካከል የተካረረው የዲፕሎማሲ ሽኩቻ እና አለመግባባቶች ከአፍሪካ ቀነድ ቃጣና ባሻገር ሁለቱን ተቀናቃኝ ኃይላትንም ጭምር ተጎጂ እንደሚያደርግ የዘርፉ ሙያተኞች ገለጡ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ኢንስትቲዩት ባለሙያዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፤ የሁለቱ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ጠብ ሁለቱንም አገራት እኩል የሚጎዳ ነው። ከመቶ ሚሊየን የላቀ ህዝብ ያላት እና በቃጣናው የአሜሪካ የደህንነት ተባባሪ ሆና ስለመቆየቷ የሚነገርላት ኢትዮጵያ የበዛ የዲፕሎማሲ ስራን በመስራት የግንኙነቶቹን ክፍተት መዝጋት ይጠበቅባታልም ተብሏል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ