የጉዞ ማስጠንቀቂያ
ረቡዕ፣ ሰኔ 7 2009ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም ለዜጎቿ ያወጣችውን የኢትዮጵያ ጉዞ ማስጠንቀቂያ አራዘመች። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ የአሜሪካን ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል አስጠንቅቋል። በአሁኑ ማስጠንቀቂያ የአሜሪካን ዜጎች እንዳይሄዱ የተከለከሉት ጎንደር እና ባህርዳር ነው። እንደ መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ መንግሥት በየጊዜው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ስለሚዘጋ በኢትዮጵያ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ለሀገሩ ዜጎች ሊደርስ እና የምክር አገልግሎት ሊሰጥ አልቻለም ። ስለ ተራዘመው ማስጠንቀቂያ የአሜሬካን ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪቃ ክፍል ቃል አቀባይን ያነጋገረው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለው።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ