የአማራ ክልል የፀጥታ ሁኔታ የዛሬ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ውሎ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 30 2015በአማራ ክልል በተለይ በምዕራብ ጎጃም ዞን ከሰሞኑ በመከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ሲደረጉ የነበሩ ውግያዎች ዛሬም በከባድ መሳሪያ ታግዘው ተጠናክረው መቀጠላቸውን የየአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በዞኑ ውግያው ዛሬም ተጠናክሮ ከቀጠለባቸው አካባቢዎች መካከል አራፋት ፣ ገንዳ ዉሃ እና ዝኩል ቃና የተባሉ አካባቢዎች ተጠቃሾች ናቸው ።የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋንበሰሜን ሸዋ ደራ የተከሰተው ግጭት በተፋላሚዎቹ መካከል በአካባቢው እየተካሄደ ያለው ውግያ ሳምንት ሳምንት ሊሞላው ሲቃረብ በተለይ በዙሪያዋ ብርቱ ውግያ እየተደረገባት ከነበረችው ፈረስ ቤት ከተማ ነዋሪው ለደህንነቱ ሽሽት መግባቱን ዶይቼ ቬለ ከነዋሪዎች ጠይቆ ተረድቷል። የመከላከያ ሰራዊትም ወደ ፈረስ ቤት መቃረቡ ተሰምቷል። በክልሉ ከምዕራብ ጎጃም በተጨማሪ ሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ አካባቢ እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት አካባቢዎች አለመረጋጋት መኖሩን ዶይቼ ቬለ ከየአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቆ ተረድቷል። በአማራ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ እና በክልሉ የጸጥታ ዘርፍ የተደረገው ሹም ሽር።በክልሉ ከከተሞች ውጭ ራቅ ብለው በሚገኙ የገጠር አካባቢዎች ስልክ ሊሰራ ባለመቻሉ ዶይቼ ቬለ በወቅቱ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ጠይቆ ማወቅ አልቻለም ። በሌላ በኩል ግን አለመረጋጋት ይታይባቸው በነበሩ እንደ ደብረማርቆስ ፣ ደብረ ታቦር እና አዴት ያሉ ከተሞች አንጻራዊ መረጋጋት እየታየባቸው እንደሚገኝ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ዓለምነው መኮንን
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ