1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

የመካከለኛዉ ምሥራቅ ግጭትና ዩናይትድ ስቴትስ

ማክሰኞ፣ መስከረም 21 2017

የእስራኤል እግረኛ ጦር «ዉስን እና ያነጣጠረ» ባለዉ ዘመቻ ዛሬ ሊባኖስ ግዛት ገብቷል።የሊባኖሱ ሒዝቡላሕና የየመኑ የሁቲ ሚሊሺዎች ባንፃሩ ቴል አቪቭን ጨምሮ በተለያዩ የእስራኤል ከተሞች ላይ ሚሳዬልና ሮኬቶች ማወንጨፋቸዉን አስታዉቀዋል

https://p.dw.com/p/4lIg2
የእስራኤል ባለሥልጣናት እንዳሉት የእግረኛ ጦራቸዉ ዘመቻ የተወሰነና ኢላማ ላይ ያተኮረ ነዉ
በታንክ፣ ጄትና ሔሊኮፕተር የተጠናከረዉ የእስራኤል እግረኛ ጦር የሊባኖስን ደቡባዊ ግዛት ከወረረ በኋላ ሲያጠቃምስል Jim Urquhart/REUTERS

የመካከለኛዉ ምሥራቅ ግጭትና ዩናይትድ ስቴትስ

 

የእስራኤል እግረኛ ጦር «ዉስን እና  ያነጣጠረ» ባለዉ ዘመቻ ዛሬ ሊባኖስ ግዛት ገብቷል።የሊባኖሱ ሒዝቡላሕና የየመኑ የሁቲ ሚሊሺዎች ባንፃሩ ቴል አቪቭን ጨምሮ በተለያዩ የእስራኤል ከተሞች ላይ ሚሳዬልና ሮኬቶች ማወንጨፋቸዉን አስታዉቀዋል።

የተለያዩ አየር መንገዶች ወደ ቴል አቪቭና ቤይሩት የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠዋል።

ምዕራባዉያን መንግሥታት ዜጎቻቸዉን ከሊባኖስ እያስወጡ ነዉ።የኔቶ አባል የሆነችዉ ቱርክና ሩሲያ የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስቴር ግን ሊባኖስ ድንበር ላይ የሚገኙ «የማጥቂያ መዋቅሮች» መፍረስ አለባቸዉ በሚለዉ ሐሳብ ከእስራኤል ጋር መስማማቱን አስታዉቋል።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ