1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝናብና ጎርፍ በሰሜን ሸዋ ያስከተለው ጉዳት

ዓርብ፣ ነሐሴ 29 2012

በአማራ ክልል በበጋው ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የግሪሳ ወፍና የአንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል። አሁን በክረምቱ ደግሞ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ከባድ ዝናብና ኃይለኛ ነፋስ ሌላ ጉዳት እያደረሰባቸው እንደሆነ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አርሶ አደሮች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3i1Dv
Äthiopien I Hagelschauer und Überschwemmung I Showa
ምስል DW/A. Mekonnen

«ለተፈናቀሉትና ጉዳት ለደረሰባቸው ርዳታ የማድረስ ጥረትም አለ»

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት ዝናብ፣ የመሬት መንሸራተትና ጎርፍ በደረሰ ሰብላቸው ላይ ጉዳት ማድረሱን አርሶ አደሮች ተናገሩ። የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ ቤት በበኩሉ ከ8ሺህ በላይ ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል መውደሙንና ከ57 ሺህ በላይ የአርሶአደር ቤተሰቦች ለጉዳት መዳረጋቸውን አስታወቋል። 700 ቤቶች በጎርፍና በነፋስ ሲፈራርሱ፣ ከ4 ሺህ በላይ የሚሆኑት ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን አመልክቷል። የሞላ ወንዝ ለመሻገር የሞከሩ 5 ሰዎች ደግሞ በውኃው መወሰዳቸው ተገልጿል።

Äthiopien I Hagelschauer und Überschwemmung I Showa
ምስል DW/A. Mekonnen

በአማራ ክልል በበጋው ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የግሪሳ ወፍና የአንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል። አሁን በክረምቱ ደግሞ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ከባድ ዝናብና ኃይለኛ ነፋስ ሌላ ጉዳት እያደረሰባቸው እንደሆነ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አርሶ አደሮች ይናገራሉ። በተለይ በሽንኩርት፣ በባቄላ በስንዴና በጤፍ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቻለው ምንዳዓ ለዶይቼ ቬለ በስልክ እንደተናገሩት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በተፈጠሩ የከባድ ዝናብ፣ የበረዶ፣ የመሬት መንሸራተት፣ የኃይለኛ ነፋስ፣ የጎርፍና የመሳሰሉት የተፈጥሮ አደጋዎች ከ8ሺህ ሄክታር በላይ በነበረ ሰብል ላይ ጉዳት ደርሷል።  
እርዳታ ለሚያስፈልጋቸውና ቤት ለፈረሰባቸው ወገኖች የኢትዮጵያ ቀይመስቀል የደብረ ብርሃን ቅርንጫፍና የዞኑ አደጋ መከላከል ጽሕፈት ቤት ድጋፍ እያደረገ እንደሆነም አስረድተዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አድማሴ በበኩላቸው አጠቃላይ በግብርና ሰብል ላይ የደረሰውን ጉዳት የሚጠና፣ ማገገም የሚችል ሰብል ካለና ቀጣይ ድጋፍ ለማድረግ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጥናት እየተደረገ ነው ብለዋል። እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብና የሚያስከትለው ጎርፍና የወንዞች ሙላት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተመሳሳይ አደጋዎች እያስከተለ እንደሆነ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። ዓለምነው መኮንን ከባሕር ዳር ዝርዝሩን ልኮልናል።  
ዓለምነው መኮንን

Äthiopien I Hagelschauer und Überschwemmung I Showa
ምስል DW/A. Mekonnen

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ