ማስታወቂያ
በዕለት ተዕለ ህይወቷ የአናቷና የታናሽ ወንድሟ ቤተሰባዊ ድጋፍ እንደማይለያትና በትምህርት ቤት ያሉ ሰዎችም በጎ አስተያየት እንደሚሰጧት ጠቅሳለች ፡፡
ታዳጊዋ አሁን ላይ የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ትናገራለች ፡፡ የሥዕል ጥበብ ዝንባሌ እንዳላትና በተወሰነ ደረጃም እሞክራለሁ የምትለው የ18 ዓመት ታዳጊ ወደፊት ዲዛይነር የመሆን ህልም እንዳላት ገልጻለች ፡፡ እንደእሷ ለጉዳት የተጋለጡ ወጣቶች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማሰብና የቻሉትን ያህል መጣር እንደሚገባቸውም ጠቅሳለች ፡፡
የእፁብድንቅ አስቻለው ወላጅ እናት ወይዘሮ እርቅነሽ ቀጸላ እፁብደንቅን ከታናሽ ወንደሟ ጋር በመሆን ወደ ትምህር ቤት በመውሰድና በማምጣት እንደሚደግፏት ይናገራሉ ፡፡ ያም ሆኖ ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እንዳሉት ነው ወይዘሮ እርቅነሽ የገለጹት ፡፡
የልጃቸው ጉዳት በህክምና ሊድን የሚችል ሥለመሆኑ በሀኪም ማስረጃ ቢረጋገጥም ባላቸው አነስተኛ ገቢ የተነሳ ለማሳካም አለመቻላቸውን የጠቀሱት ወይዘሮ እርቅነሽ “ ልጄ እንድትድን እፈልጋለሁ ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለው አቅም እንዲደግፈኝ እማጸናለሁ “ ብለዋል ፡፡ #ዝምታሰባሪአዳጊሴቶች #GirlzOffMute
ዘገባ: ሊሻን ዳኜ
ቪድዮ: ሸዋንግዛው ወጋየሁ