በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች
እሑድ፣ ጥቅምት 25 2016ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭቶችና በሌሎች ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ3.14 ሚሊዮን በልጧል። ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በምህጻሩ ኢሰመኮ በቅርቡ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በሄደበት በአሁኑ ወቅት በየተጠለሉባቸው አካባቢዎች የሚደርሱባቸው የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተባብሰዋል። ኮሚሽኑ በዘገባው እንዳጋለጠው ተፈናቃዮች ተገቢውን እርዳታና መጠለያ በአስፈላጊው ጊዜ ባለማግኘትና በፀጥታ ችግሮችም መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶቻቸው እየተጣሱ ነው።ተፈናቃዮች በርዳታ እጦት እየተሰቃዩ ነዉድንገት ተፈናቅለው በማያውቁትና መጠለያ ሊባሉ በማይችሉ ስፍራዎች ለብዙ ጊዜያት የቆዩ በርካቶች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ችግሮቻቸው እየተባባሱ እንጂ እየቀነሱ አልሄዱም። በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለከፋ ችግር ከተጋለጡት የአብዛኛዎቹ ፍላጎት ወደ ቀድሞው ቀያቸው መመለስ ነው።ወደ ቀያቸው ለመሄድ ቢፈልጉም በቀድሞ መኖሪያቸው የፀጥታ ዋስትና አለመኖር ያሰጋቸዋል።
በሌላ በኩል በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አከባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተጠለሉትን ወደ መጡበት ለመመለስ በቅርቡ የአማራ እና ኦሮሚያ ክልል አመራሮች መስማማታቸውን አስታውቀዋል። የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ፈተናዎች በአጠቃላይ ፣የሚደርሱባቸው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መገለጫዎቹ እና ዘላቂ መፍትሄዎቹ የዛሬው እንወያይ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው።የሆሮጉድሩ ተፈናቃዮች ሮሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ወይዘሪት እንጉዳይ መስቀሌ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የስደተኞች የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና ፍልሰተኞች መብቶች ክፍል ሃላፊ እንዲሁም አቶ ያሬድ ኃይለማርያም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ሥራ አሥኪያጅ ይወያያሉ።
ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ
ኂሩት መለሰ