1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሁለት የአማራ ከተሞች በረራዉን ሰረዘ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2015

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሁለት የአማራ ክልል ከተሞች የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ዛሬ አስታወቀ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል ያለው ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸው ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/4Ukq7
Fluggesellschaft Ethiopian Airlines | Frachtflugzeug Boeing 777F
ምስል Wolfgang Minich/picture alliance

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሁለት የአማራ ክልል ከተሞች የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ዛሬ አስታወቀ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአማራ ክልል ያለው ግጭት መባባስ እንዳሳሰባቸው መናገራቸዉን ዛሬ የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። በፌደራል ወታደሮች እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ምክንያት ብሪታኒያ እና ስፔን ለዜጎቻቸው የጸጥታ ማስጠንቀቂያ ማዉጣታቸዉም ተመልክቷል። የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ የአማራ ሚሊሻ ፋኖ በላሊበላ የሚገኘውን አየር ማረፊያ መቆጣጠሩን መግለፁን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።  
ዜና ምንጬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ አሸናፊ ዘርዓይ «የጎንደር እና የላሊበላ አውሮፕላን ማረፊያዎች እና በረራዎች ተቋርጠዋል» ሲሉ መናገራቸዉን እና በረራዉ የተሰረዘበትን ምክንያት ግን እንደማያውቁ መናገራቸዉን ጠቅሷል። 

 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ