1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ጦርነት የሚሸከም ጫንቃ ይኖራታል?

እሑድ፣ ነሐሴ 22 2014

ዳግም ጦርነት አገርሽቷል። ፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ በአጭሩ ህወሃት ከዓመት በላይ የተሻገረ ጦርነት ውዝግባቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በድርድር ለመፍታት መዘጋጀታቸው ሲሰማ ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ተስፋ ደብዝዟል።

https://p.dw.com/p/4G6T5
Tigray-Krise in Äthiopien
ምስል UGC/AP/picture alliance

እንወያይ፦ ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ጦርነት የሚሸከም ጫንቃ ይኖራታል?

ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈራ የነበረው ጦርነት ዳግም ማገርሸቱ ብዙዎችን አደናግጧል። ፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ህዝባዊ  ወያነ ሃርነት ትግራይ በአጭሩ ህወሃት ከዓመት በላይ የተሻገረ ጦርነት ውዝግባቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በድርድር ለመፍታት መዘጋጀታቸው ሲሰማ ተፈጥሮ የነበረው የሰላም ተስፋ ደብዝዟል። በፖለቲካ መሪዎቹ መካከል የሚካሄደው ጦርነት በህዝብ እና በሀገር ጫንቃ ላይ እንደመሆኑ መከራይ ይቀልልነት ዘንድ አብዛኛው ዜጋ የሰላም አማራጭ እንዲፈለግ ድምጹን እያሰማ ነው። ያለፈው የጦርነት ጠባሳ ሳያገግም የረገፈው ወገንም መርዶ እንኳን በወጉ ሳይጠቃለል፤ የወደመው የደሀይቱ ሀገር መሠረተ ልማት ተጠግኖ ሳያበቃ ዳግም ውጊያ መቀስቀሱ በቀጣይ ሊከተል የሚችለውን ውድመት እና ጉዳት መሸከሚያው ጫንቃ ይኖር ይሆን? የመከረኛው ሕዝብ ስቃይስ መቼ ያበቃል? በሚሉ ነጥቦችን በማንሳት ዶቼ ቬለ  ውይይት አካሂዷል። አራት ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን ያካፈሉበት ሙሉውን ውይይት ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሸዋዬ ለገሠ