1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከሩጫው ዓለም ራሴን የማግለያ ጊዜው አይታወቅም አለ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2016

አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከሩጫው ዓለም ራሴን የማግለያ ጊዜው አይታወቅም አለ። ቀነኒሳ በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንዳለው አሁን ጊዜው በፓሪስ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ ትኩረት ማድረግ እና ውጤት ማምጣት ነው። ከነገ በስትያ ቅዳሜ ለሚደረገው የማራቶን ውድድርም ተገቢውን ዝግጅትn ማድረጉን ገልጿል።

https://p.dw.com/p/4jGAj
Flash-Galerie Leichtathletik Weltmeisterschaft 2009 Berlin
ምስል picture-alliance/ dpa

ሩጫ ለማቆም ጊዜው አይታወቅም ፤ ቀነኒሳ በቀለ

አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከሩጫው ዓለም ራሴን የማግለያ ጊዜው አይታወቅም አለ። ቀነኒሳ በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ እንዳለው አሁን ጊዜው በፓሪስ ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ ትኩረት ማድረግ እና ውጤት ማምጣት ነው። ከነገ በስትያ ቅዳሜ ለሚደረገው የማራቶን ውድድርም ተገቢውን ዝግጅትn ማድረጉን ገልጿል።

ሌላኛው የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌት ታምራት ቶላም በተመሳሳይ ለውድድሩ መዘጋጀቱን ገልጿል። ሲሳይ ለማ በጉዳት ከቡድኑ በመቀነሱ ምክንያት ተክቶት የገባው ታምራት የሚጠበቅብኝን ለማድረግ ተዘጋጅቻለሁ ብሏል። 

ቀነኒሳ በቀለ
አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከሩጫው ዓለም ራሴን የማግለያ ጊዜው አይታወቅም አለምስል AP

ከጉዳት የተመለሰው ቀነኒሳ በቀለ የበርሊን ማራቶንን አሸነፈ

 የኢትዮጵያ የወንዶች የማራቶን ብሄራዊ ቡድን ትናንት ረቡዕ ጠዋት ነበር ፈረንሳይ ፓሪስ የደረሰው ። ቡድኑ ፓሪስ ሻል ደጎል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በስፍራው የተገኘችው የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት እና የኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝደንት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርጋለታለች።

ለንደን ማራቶን፥ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ፈይሳ ሊሌሳ

በማራቶን የምንጊዜም ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ባለቤት እና በቅርቡ የ21ኛ ክፍለ ዘመን የአፍሪቃ ቀዳሚ ምርጥ አትሌት ቀነኒሳ በቀለን ጨምሮ አትሌት ታምራት ቶላ እና ዴሬሳ ገለታ በውድድሩ ተሳታፊ ናቸው።  የማራቶን ቡድኑ በተለይ ከኬንያውያን ተወዳዳሪዎች ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቃቸው ይገመታል። የወንዶች የማራቶን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ይደረጋል።

ኃይማኖት ጥሩነህ

ታምራት ዲንሳ 

ሸዋዬ ለገሰ