የአዲስ አበባው የተቃውሞ ሰልፍ
ሰኞ፣ ግንቦት 23 2013ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የምታደርገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ትናንት በአዲስ አበባ የተደረገው ሰልፍ ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። በአንድ ወገን ሰልፉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል ያሉ እንደመኖራቸው በሌላ ወገን ደግሞ ሰልፉ መካሄዱ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የወሰደቻቸውን እርምጃዎች ቆም ብላ እንድታጤን የሚረዳ ነው በማለት የደገፉም አሉ።ሰልፉን የተቃወሙ ሁለት ፓርቲዎች በሰልፉ ላይ ተቃዋሚዎች ዩናይትድ ስቴትስ በውስጥ ጉዳይ እንዳትገባ ጠይቆ ሌሎች ኃያላን አገሮች ግን እንዲገቡ የመጠይቅ አዝማሚያ መታየቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ የኃያላኑ ግብግብ እንዲፈጠር የሚያበረታታ ነው ሲሉ ነቅፈዋል።አንድ ምሁር ደግሞ ተቃውሞን ማሰማት አሜሪካ ራሷ የምትፈቅደው መብት በመሆኑ ሰልፉ መደረጉ ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ