Eshete Bekele/ MMTረቡዕ፣ ነሐሴ 22 2016ወንጂ ሸዋ፣ መተሐራ፣ ፊንጫ፣ ከሰም እና ጣና በለስ ፋብሪካዎች በ2016 ያመረቱት 124,097 ቶን ስኳር እንደሆነ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዐስታውቋል። ይኸ የሚሸፍነው 10% የኢትዮጵያን የስኳር ዓመታዊ ፍላጎት ብቻ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ኸርነስት ኤንድ ያንግ በተባለ አማካሪ ኩባንያ ያሠራው የገበያ ጥናት የሀገሪቱ የስኳር ፍላጎት በጎርጎሮሳዊው 2020/2021 መጨረሻ 1.2 ሚሊዮን ቶን እንደሚገመት ያሳያል። መንግሥት እስከ ጥር ስምንት ስኳር ፋብሪካዎችን በመሸጥ የፈሰሳባቸውን በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር መመለስ እና የግል መዋዕለ-ንዋይ ወደ ዘርፉ ለመሳብ አቅዷል።