ትራምፕ በሪያድ ንግግራቸው
እሑድ፣ ግንቦት 13 2009ማስታወቂያ
ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ የ50 አገራት መሪዎች እና ተወካዮች በተገኙበት ባደረጉት ንግግር የእስልምና እምነት ተከታይ መሪዎች፤ አሸባሪዎችን ሊያጠፉ እንደሚገባ በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ዩናይትድ ስቴትስ እና ሳዑዲ አረቢያም ቅዳሜ ዕለት ወዲያው ተፈፃሚ የሚሆን የ 110 ቢሊዮን ዶላር የጦር ግዢ ስምምነት ተፈራርመዋል። በ10 ዓመት እድሜ ውስጥ ደግሞ ሳዑዲ ከዩናይትድ ስቴትስ 350 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ትገዛለች።
የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት አስመልክቶ ሳውዲ አረቢያ የሚገኘው ወኪላች ስለሺ ሽብሩ ተጨማሪ መግለጫ ሰጥቶናል።
ስለሺ ሽብሩ
ልደት አበበ