1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባይደን ለሁለተኛ ዘመነ ስልጣን እወዳደራለሁ አሉ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2015

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት ለሁለተኛ ዘመነ ስልጣን እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። ባይደን የምረጡኝ ዘመቻ መርሃቸዉ «ስራችንን እንጨርስ» የሚል መሆኑንም አስታዉቀዋል። የባይደን ተቀናቃኝ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና ሪፐብሊካኑ ዶል ትራምፕ ሳይሆኑ አይቀርም ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4QY4y
USA, Accokeek | Präsident Joe Biden
ምስል Patrick Semansky/AP/picture alliance

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት ለሁለተኛ ዘመነ ስልጣን እንደሚወዳደሩ አስታወቁ።  ባይደን የምረጡኝ ዘመቻ መርሃቸዉ«ስራችንን እንጨርስ» የሚል መሆኑንም አስታዉቀዋል። ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ በ 80 ዓመታቸዉ ስልጣን ላይ የሚገኙ የመጀመርያዉ አዛዉንት መሪ ናቸዉ። ባይደን ለሁለተኛ ዘመነ ስልጣን ተወዳድረዉ ከተመረጡ ስልጣናቸዉ የሚያበቃዉ 86 ዓመታቸዉን ሲይዙ ይሆናል። በዚህም ምክንያት ብዙ የዩናይትድ ስቴትስ መራጮች ባይደን ለሁለተኛ ዙር ምርጫ ሊወዳደሩ ነዉ የሚለዉን በጥብቅ ይነቅፋሉ። የባይደን ተቀናቃኝ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና ሪፐብሊካኑ ዶል ትራምፕ ሳይሆኑ አይቀርም የሚሉ ዘገቦችም እየወጡ ነዉ።

 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ