1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

በአሜሪካ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ብርቱ ፉክክር የሚደረግባቸው ሦስት ግዛቶች አሸነፉ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 27 2017

ዓለም የአሜሪካን የ2024 ፕሬዝዳንዊ ምርጫ በዐይነ ቁራኛ እየተከታተለ ነው። ዶናልድ ትራምፕ እና ካማላ ሐሪስ ብርቱ ፉክክር በማድረግ ላይ ናቸው። ኃይለኛ ውድድር ይደረግባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት ግዛቶች መካከል ዶናልድ ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ፣ በኖርዝ ካሮላይና እና በጆርጂያ አሸንፈዋል።

https://p.dw.com/p/4mgey
የአሜሪካ የ2024 ፕሬዝዳንዊ ምርጫ
ዓለም የአሜሪካን የ2024 ፕሬዝዳንዊ ምርጫ በዐይነ ቁራኛ እየተከታተለ ነው።ምስል Alex Wong/Getty Images

በአሜሪካ የ2024 ፕሬዝዳንዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ ኃይለኛ ፉክክር የሚደረግባቸውን ሦስት ግዛቶች አሸንፈዋል። ትራምፕ ፔንሲልቫኒያ፣ ኖርዝ ካሮላይና እና በጆርጂያ አሸናፊ ናቸው።

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በፍሎሪዳ፣ ኦሓዮ፣ ቴክሳስ እና አይዋ አሸንፈዋል። 

ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሐሪስ በካሊፎርኒያ፣ ማሳቹሴትስ፣ ቬርሞንት፣ ሮድ ደሴት፣ ኬኔትከት፣ ሜሪላንድ፣ ኢሊኖይ እና ኒው ዮርክ አሸናፊ ናቸው። 

የምርጫውን ውጤት ይወስናሉ ከሚባሉ ግዛቶች መካከል በሆኑት ዊዝኮዚን እና ሚሺጋን አሁንም የድምጽ ቆጠራ በመካሔድ ላይ ይገኛል።