1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሃገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር

ሐሙስ፣ ነሐሴ 23 2011

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ኤኮኖሚ መገንባትንም ያካታታል ብለዋል።የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው ባለፉት 15 ዓመታት በኤኮኖሚው ዘርፍ ተመዝግበዋል ካሏቸው በጎ ውጤቶች ጎን የፍትሃዊነት መጓደልና የማክሮ ኤኮኖሚ መዛባት ችግር እንደነበርም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3Oi6K
Äthiopien Addis Abeba  Home grown economic reform Forum | Demeke Mekonnen
ምስል DW/Y. Gebrezihaber

ሃገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር
ፈጣን የሚባለው የኢትዮጵያ እድገት ዘላቂ እንዲሆን ለወጣቱም የተሻለ የሥራ እድል እንዲፈጠር ታስቦ የተዘጋጀው ሃገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ይፋ ተደርጓል።በስብሰባው ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ኤኮኖሚ መገንባትንም ያካታታል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ባሰሙት ንግግር ባለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ በኤኮኖሚው ዘርፍ ተመዝግበዋል ካሏቸው በጎ ውጤቶች ጎን የፍትሃዊነት መጓደልና የማክሮ ኤኮኖሚ መዛባት ችግር እንደነበርም ገልጸዋል።በስብሰባው ላይ ልዩ ልዩ ምሁራን የግሉ ዘርፍ ተወካዮች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።  የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ስብሰባውን ተከታትሏል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
 ተስፋለም ወልደየስ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ