ዳግም የጀርመንን ምርጫ ያስተናገደችዉ በርሊን ከተማ
ሰኞ፣ የካቲት 4 2016ማስታወቂያ
በርሊን ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች በ 2021 ዓመት ተካሄዶ የነበረዉ ምርጫ በድጋሚ ተካሄደ። ወደ 500 ሺህ ግድም መራጮች የተሳተፉበት ይህ ምርጫ ዳግም የተካሄደዉ፤ በ 2021 ዓመት በተካሄደዉ ምርጫ አንዳንድ ድርጊቶች ሳይሟሉ በመቅረታቸዉ የተጓደለ ምርጫ ተካሄዷል ፤ በሚል ዳግም እንዲካሄድ በፍርድ ቤት በመወሰኑ ነዉ። የዛሬ ሦስት ወር ላይ በፍርድ ቤት ምርጫዉን በተሟላ ሁኔታ ሳያካሄዱ ቀርተዋል በተባሉ በአንዳንድ የበርሊን ክፍለ ከተማዎች ዳግም እንዲያካሂዱ ወስኖ ነበር። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ከስፍራዉ እንደነገረን፤ ትናንት እሁድ በተካሄደዉ የድጋሚ ምርጫ ላይ ወደ 500 ሲህ የሚሆኑ ሰዎች ተሳትፈዋል። ይህ ትናንት የተካሄደዉ ህግና ስርአቱ በዲሞክራሲ ስህተት ሲፈፀም ተስተካክሎ እንደገና መሰራቱን የሚያሳይ፤ ሁለተኛ ምርቻ አንድ ጊዜ ተካሂዷል ተብሎ የተፈፀመዉ ስህተት የማይሰተካከልበት ሳይሆን ተስተካክሎ እንደገና ምርጫ መደረግ መቻሉን የሚያሳይ ነዉ ብሏል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
እሸቴ በቀለ