የኮሬ ማኅበረሰብ አባላት አቤቱታ
ሰኞ፣ መጋቢት 30 2011ማስታወቂያ
የማኅበረሰቡ አባላት ትናንት በጉዳዩ ላይ በሀዋሳ ከተማ ባካሄዱት ውይይት ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች በማኅበረስቡ አባላት ላይ የግድያ እና መፈናቀል ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛሉ ብለዋል። መንግሥት በአካባቢው የሚንቅሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎቸን ትጥቅ እንዲያስፍታ ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመልስ እና የሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎችም ካሣ እንዲከፍል ጠይቀዋል። ውይይቱን የተከታተለው የሀዋሳው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል።
ሽዋንግዛው ወጋየሁ