1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጋድ የሰላም ጥረት በኢትዮጵያ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 26 2015

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈራረሙ ከስምምነቱ በፊትም ሆነ በኋላ ስኬት የታየበት ያለውን የማግባባት ሥራ ማከናወኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት ( ኢጋድ ) አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/4S9yC
Äthiopien | IGAD
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና የኢጋድ የሰላም ጥረት

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈራረሙ ከስምምነቱ በፊትም ሆነ በኋላ ስኬት የታየበት ያለውን የማግባባት ሥራ ማከናወኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት ( ኢጋድ ) አስታወቀ።
ይህ የመንግሥታት ቀጣናዊ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራቱ የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጡ ፣ የኢኮኖሚ ትብብሮችን እንዲያጠናክሩ እና በአካባቢው ሰላምና ደህንነት እንዲጠናከር ይሠራል።
የድርጅቱ የፀጥታ እና ደህንነት ዘርፍ ፕሮግራም ዳይሬክተር እና የኢጋድ ተልእኮ በኢትዮጵያ ኃላፊ ኮማንደር አበበ ሙሉነህ በተለይም ለዶቼ ቬለ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ ከሚጠራው ቡድን ጋር ዛንዚባር ላይ በተደረገው የሰላም ውይይት ላይ የማቀራረብ እና የማወያየት ሥራ አከናውኗል፣ አሁንም ይህንን ሥራ እየገፋበት ነው።
የኢትዮጵያ እና የሱዳን የአልፋሽጋ የድንበር ውዝግብ ወደለየለት ጦር መማዘዝ እንዳይሸጋገርም ኢጋድ የሁለቱን ሀገሮች መሪዎች ኬንያ ላይ በማገናኘት ጉዳዩ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያገኝ እገዛ ማድረጉም ተገልጿል።
ከ1986 ዓ. ም ጀምሮ ተቋማዊ ለውጥ ካደረገ ወዲህ በዋናነት በአባል ሀገራቱ ውስጥ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ፣ የኢኮኖሚ ትብብሮችን የማጠናከር እና ሰላምና ደህንነት በእንዲጠበቅ ለማድረግ ተጨባጭ ጥረቶችን እያደረገ ነው የሚባልለት ኢጋድ በሰሜን እና ደቡብ ሱዳን መካከል የነበረን ስምምነት እንዲፈረም በማድረግ ፣ የጦር አበጋዞች የሚያተራምሷት ሶማሊያ ላይ  የሽግግር ፌዴራላዊ  መንግሥት በማቋቋም ፣ በደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ ጣልቃ በመግባት የመሪዎች ጉባኤ በማካሄድ የማቀራረብና የማስማማት ሥራዎችን መስራቱን እንዲሁም
በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ሳይቋጭ የዘለቀው የአልፋሽጋ የድንበር ውዝግብ ወደለየለት ጦርነት እንዳይሸጋገር ከጀርባ ሆኖ ውጤት የተገኘባቸው የተባለለትን የዲፕሎማሲ ጥረት ማድረጉን ድርጅቱ አስታውቋል።
በሀገራት የሰላምና ደህንነት የውስጥ ገዳይ ጭምር ጣልቃ በመግባት ላይ መሆኑን የገለፁት በድርጅቱ የፀጥታ እና ደህንነት ዘርፍ ፕሮግራም ዳይሬክተር እና የኢጋድ ተልእኮ በኢትዮጵያ ኃላፊ ኮማንደር አበበ ሙሉነህ በቅርቡ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት ውስጥ በማስማማት ሂደት ላይ ኢጋድ "ከፍተኛ ድርሻ ነበረው" ብለዋል።
በተመሳሳይ ሱዳን ውስጥ በሀገሪቱ መሪዎች አልመግባባት የተቀሰቀሰው የከተማ ውስጥ ጦርነት እንዲቆም የጎረቤት ሀገራት መሪዎችን በመጥራት ችግሩን ለመፍታት "ግንባር ቀደም ሆኖ ጥረት እያደረገ ነው"። ብለዋል።
አካባቢው ትርምስና ግጭት የማይለየው መሆኑና የብዙ የውጪ ኃይሎች ጣልቃ ገብ ፍላጎቶች መበራከት ክፉኛ ሥራውን ባይገታው ኢጋድ በአባል ሀገራቱ ሕዝቦች እና መንግሥታት መካከል ቀጣናዊ ውህደትን መፍጠር ዋና አላማው መሆኑን የድርጅቱ ባለሥልጣን ገልፀዋል።
ኢጋድ እንደ አፍሪካ ሕብረት ሁሉ ጠንካራ ሥራዎችን መፈፀም የማይችል ስብስብ ነው በሚል ከተለያየ አቅጣጫ ትችት ይሰነዘርበታል። ኮማንደር አበበ ሙሉነህ የድርጅቱ የፀጥታ እና ደህንነት ዘርፍ ፕሮግራም ዳይሬክተር እና የኢጋድ ተልእኮ በኢትዮጵያ ኃላፊ እንደሚሉት ግን ኢጋድ እንዲያውም " በጥሩ ሁኔታ እያደገ ነው" ብለዋል።
ዋና መሥሪያ ቤቱን ጅቡቲ ውስጥ ያደረገው ኢጋድ ኢትዮጵያን፣ ሁለቱን ሱዳኖችን ፣ ሶማሊያን፣ ኡጋንዳንና ኬንያን ያቀፈ ሲሆን ኤርትራ በአሁን ወቅት ከስብስቡ ተሳትፎ የላትም።   
ሶሎሞን ሙጬ

Äthiopien Addis Abeba | IGAD Friedensbemühungen - Commandor Abebe Muluneh
ኮማንደር አበበ ሙሉነህምስል Solomon Muchie/DW
Äthiopien Addis Abeba | IGAD Friedensbemühungen - Commandor Abebe Muluneh
ኮማንደር አበበ ሙሉነህምስል Solomon Muchie/DW

ታምራት ዲንሳ