ኢትዮጵያና ኤርትራን ያወገዘው የአሜሪካን መግለጫ
ሰኞ፣ ግንቦት 9 2013ማስታወቂያ
የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ላይ የሚያራምደውን የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ በግልፅ አለማስቀመጡ ኢትዮጵያን ለተደጋጋሚ ተፅዕኖ እየዳረጋት መሆኑን ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሰላም ሚኒስቴር ባለሥልጣን ገለፁ።ባለፈው ቅዳሜ የአሜሪካን መንግሥት ባወጣው «የኤርትራና የኢትዮጵያን መንግሥታት በሚያወግዝ መግለጫ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ባለሥልጣኑ ፣ ስለ ኢትዮጵያ የሚወጡ የተሳሳቱ መረጃዎችና የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ያልተጣራ የመረጃ ስርጭት እውነትን እያናጋ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንድታሳርፍ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውን ገልጸዋል።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መንግሥታት የሚወገዝ እና ተቀባይነት የሌለው ያለውንና በትግራይ እየተፈፀመ ነው ያለውን ድርጊት ለማስቆም የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ