የአሜሪካ የምርጫ ውጤት እና የፕሪቶሪያው ስምምነት
ረቡዕ፣ ጥቅምት 27 2017ማስታወቂያ
በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ያሸነፉት መሪ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በምሉእነት እንዲተገበር እንዲሠሩ እንደሚጠብቁ ለዶቼ ቬለ አስተያየታቸውን የሰጡ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች አመለከቱ። ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ ላይ የሰሜኑን ጦርነት ለማስቆም በኢትዮጵያ መንግሥት እና ህወሓት መካከል ከተደረሰው የሰላም ስምምነት ጀርባ እንዳለች ሀገርና ሌሎች ጉዳዮችን በመጥቀስ፥ በርካቶች በትግራይ ክልል የአሜሪካንን ምርጫና ውጤት በትኩረት መከታተላቸውን ይናገራሉ። አሜሪካ በኢትዮጵያ እና በአጠቃላይ አፍሪካ ቀንድ ካላት ተፅእኖ አኳያ አስተያየታቸውን የሰጡት አካላት፥ ሀገሪቱ በቀጣይም በቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም ሰብአዊ ድጋፍ ላይ ገንቢ አብርክቶዋ እንዲቀጥል ይጠብቃሉ። ከመቀለ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት አሰባስበናል።
ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ