በጀርመን የፀረ አይሁድ እንቅስቃሴ እና የመንግስት የጸና አቋም
ዓርብ፣ ጥቅምት 9 2016ማስታወቂያ
ያዝነዉ ሳምንት ሃሙስ በርሊን ውስጥ በአይሁዳውያን ምኩራብ ላይ የፀረ አይሁዳውያን ጥቃት ከደረሰ በኋላ የጀርመን መንግስት በፀረ አይሁዳውያን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ በሚያደርጉ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል። መዲናዪቱ በርሊን ውስጥ ምንም እንኳ የከፋ ጉዳት ባያደርስም የጸረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ አራማጆች ተቀጣጣይ ነገር መወርወሩን ተከትሎ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስን ጨምሮ ፖለቲከኞች መረር ያለ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል። በጀርመን መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀውን ሃማስን መደገፍም ሆነ እስራኤልን መቃወም በህግ ጭምር በታገደባት ጀርመን ባለፉት ቀናት ፍልስጥኤማውያኑን የሚደግፉ እና እስራኤልን የሚያወግዙ ሰልፎች መታየታቸውን ተከትሎ በሰልፉ የሚሳተፉትንም ሆነ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል። በእስራኤል ሃማስ ጦርነት ጀርመን የምትከተለው ፖሊሲባለፈው ረቡዕ በበርሊን የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ እና ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል የተባሉ ከ170 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቧል። ጀርመን ከዚህ በኋላ የዜግነት ጥያቄ ለሚያቀርቡ በእስራኤል ህልውና የሚምኑ መሆን እንዳለባቸውም ከወዲሁ እየገለጸች ነው።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ