1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰሜን ሸዋው የደራ ግጭት

ሐሙስ፣ ነሐሴ 25 2015

ከአማራ ክልሉ የፀጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ከኦሮሚያ ክልል ደራ ወረዳ ጋር በሚዋሰንበት አከባቢ ከእሁድ ጀምሮ በተፈጠረው ግጭት በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን አንድ ባለሥልጣን ተናገሩ።«ደራ ወረዳ ውስጥ ፋኖ ብለው እራሳቸውን አደራጁ»ያሏቸው አካላት የተለያዩ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ሲሉ እኚሁ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ባለስልጣን ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/4VnyA
ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወደ አቢቹ እና ኘዓ ወረዳ በገቡ ታጣቂዎች እና የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አስከባሪዎች መካከል እንደሆነ ተገልጾም ነበር። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪ እና ባለስልጣን  በግጭቱ በትንሽ ግምት ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸውንም ገልጸው ነበር።
በአማራ ክልል አለመረጋጋቱ ከተከሰተ ወዲህ በተደጋጋሚ ግጭት የሚስተዋልበት የሁለቱ ክልሎች ሌላኛው አዋሳኝ ስፍራ በሁለቱ ክልሎች ሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ በሆነው አቢቹና ኘዓ ወረዳ አከባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ በነበረ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኝ እና አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ መናገራቸውም ይታወሳል። ምስል Seyoum Getu/DW

በሰሜን ሸዋ ደራ የተከሰተው ግጭት

ከአማራ ክልሉ የፀጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ከኦሮሚያ ክልል ደራ ወረዳ ጋር በሚዋሰንበት አከባቢ ከእሁድ ጀምሮ በተፈጠረው ግጭት በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን አንድ ባለሥልጣን ተናገሩ። አንድ የአከባቢው ባለስልጣን ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፣ባለፈው እሁድ የፋኖ ታጣቂዎች የክልሉን ወሰን ጥሰው በመግባት ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ሰኞ እለት በመከላከያ ሰራዊት እና በአከባቢው ሚሊሻ በተወሰደ እርምጃ ወሰኑን ጥሰው ገብተው ነበር ባሏቸው በርካታ ታጣቂዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።ባለስልጣኑ በአሁኑ ጊዜ ከተወሰኑ አከባቢዎች ውጪ ወረዳው ተረጋግቷል ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ውስጥ ፋኖ ብለው እራሳቸውን አደራጁ ያሏቸው አካላት ባለፈው እሁድ በሦስት ቀበሌ ውስጥ ገብተው በአከባቢው ማህበረሰብ ላይ ጥቃት በማድረስ ትጥቅ የማስፈታት እና የተለያዩ ጥቃቶችን ፈጽመዋል ያሉት እኚህ ስማቸው እንዳይጠቀስ ጠይቀውን አስተያየታቸውን የሰጡን ባለስልጣን በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ የታጣቂዎቹን እንቅስቃሴ መግታት መቻሉን ገልጸዋል፡፡ እንደ ባለስልጣኑ አስተያየት እነዚህ ጥቃት አደረሱ የተባሉት ታጣቂዎች ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ የደራ አጎራባች ወረዳዎች የተውጣጡ ናቸው ብለዋል፡፡ ታጣቂዎቹ የተሳሳተ ያሉትን ህዝብን የማነሳሻ ቅስቀሳዎች ተጠቅመው ለግጭት አነሳስተዋል ሲሉም ከሰዋቸዋል፡፡ በለስልጣኑ አክለው እንዳብራሩትም እሁድ የክልሉን ወሰን ጥሰው ገብተው ነበር ባሏቸው ታጣቂዎች ላይ በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ የማጥቃት እርምጃ በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸውን ነው ያመለከቱት፡፡ በአማራ ክልል የመከላከያና የፋኖ ግጭት


ታጣቂዎቹ በደረሱባቸው ቀበሌያት ንብረት እና ሰው ላይ ጥቃት በመፈጸምም ከሷቸዋል፡፡ ወረዳው አሁን በመደበኛ ስራ ላይ መሆኑንም በማንሳት አስተዳደራቸው የበለጠ ሰላሙን ለማረጋገት እንደሚሰራም ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለምልልስ ተናግረዋል፡፡ በአማራ ክልል አለመረጋጋቱ ከተከሰተ ወዲህ በተደጋጋሚ ግጭት የሚስተዋልበት የሁለቱ ክልሎች ሌላኛው አዋሳኝ ስፍራ በሁለቱ ክልሎች ሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ በሆነው አቢቹና ኘዓ ወረዳ አከባቢ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ ወረዳ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ በነበረ የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኝ እና አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ለዶይቼ ቬለ መናገራቸውም ይታወሳል። ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወደ አቢቹ እና ኘዓ ወረዳ በገቡ ታጣቂዎች እና የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አስከባሪዎች መካከል እንደሆነ ተገልጾም ነበር። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪ እና ባለስልጣን  በግጭቱ በትንሽ ግምት ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸውንም ገልጸው ነበር።የተፈናቃዮች መብዛት ያሳሰበው የሰሜን ሸዋ ዞን
ዛሬ ከዚሁ አከባቢ አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ ነዋሪ እንዳመለከቱት ግን ከቅዳሜ ወዲህ በዚህ አከባቢ የተፈጠረ ግጭትም ሆነ ውጥረት አልተስተዋለም፡፡

 ስለ እነዚህ አከባቢዎች ግጭት ከሁለቱም ክልሎችም ሆነ ከፌዴራል መንግስት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም፡፡ ዶይቼ ቬለ ስለ አከባቢው ትክክለኛ ሁኔታ ከገለልተኛ አካልም ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ 
በአማራ ክልል በኩል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ ነዋሪ በበኩላቸው አሁንም በአከባቢው የተረጋጋ ነገር አለመኖሩን አስረድተው ለችግሩ ፖለቲካዊ እልባት እንዲፈለግለት የጠየቁበትን አስተያየት ሰጥተውናል፡፡

“አሁን የመከላከያ ጦሩ ቅዳሜ እዚህ አከባቢ በኛ በኩል ካለፈ ወዲህ ወደ እኛ የመጣ ጥቃት የለም፤አሁን ሰላም ነው እኛ ጋር ያለው፡፡ ለሚ እና እንዋሪ ወደሚባሉ አከባቢዎች ነበር ቅዳሜ መከላከያ ሰራዊቱ ያመራው፡፡ ከቅዳሜ ወዲህ እኛ ጋ ተረጋግቷል ምንም የለም፡፡”በአማራ ክልል በኩል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ ነዋሪ በበኩላቸው አሁንም በአከባቢው የተረጋጋ ነገር አለመኖሩን አስረድተው ለችግሩ ፖለቲካዊ እልባት እንዲፈለግለት የጠየቁበትን አስተያየት ሰጥተውናል፡፡ስለ እነዚህ አከባቢዎች ግጭት ከሁለቱም ክልሎችም ሆነ ከፌዴራል መንግስት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም፡፡ የተፈናቃዮች መብዛት ያሳሰበው የሰሜን ሸዋ ዞንዶይቼ ቬለ ስለ አከባቢው ትክክለኛ ሁኔታ ከገለልተኛ አካልም ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ ከሰሞኑ በተናጠል መግለጫ ያወጡት የአሜሪካ መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግን የአማራ ክልሉ ግጭት አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው መፍትሄ እንዲበጅለት መጠየቃቸውም አይዘነጋም፡፡
ስዩም ጌቱ 
ኂሩት መለሰ